ሰበር ዜና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጥቃት ቀጥሏል

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጥቃት ቀጥሏል


ከወለጋ ቄለም 160 ኪ/ሜትር እርቀት ላይ በኢትዮጵያና በሱዳን አዋሳኝ ልዩ ስሙ ቢልበል ተብሎ በሚጠራዉ ስፍራ በትናንትናዉ እለት ከምሽቱ 6፡45 ጀምሮ ከባድ ዉጊያ በማድረግ ከ 60 በላይ የወያኔ ሰራዊት አባላትን በመደምሰስ 18 ወታደሮችን ማቁሰሉ ተረጋገጠ።
በቦንሳ ሰባ ፣ በዶ/ ኑሮ ደደፎ ፣ በአቶ ድሪባ ወርዶፋ ፣ እንዲሁም በብደታ ሹኬ ተነጣጥሎ የነበረዉ የኦነግ የነጻነት ትግል ወደ ጥምረት ከመጣ ብኍላ በሐረርና በሞያሌ እንዲሁም በደንቢዶሎ ጥቃት ሲፈጽም የነበረዉ የኦነግ ህብረት ሐይል በወለጋ በኩል ያደረሱዉ ጉዳት ከበድ ያለ መሆኑን መረጃዎች የሚጠቁሙ ሲሆን ጥቃቱን ለመከላከል በስፍራዉ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘዉ ጸረ ሽምቅ ሐይልን ለማጠናከር ተጨማሪ ፌደራል ፖሊሶች ተልኮለታል።

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *