ከሀዲው ሞላ አስገዶም በጠና መታመሙ ተነገረ

  • mqdefault
  • በአራት ታላላቅ የነፃነት ድርጅቶች ጥምረት የተቋቋመውን የአገር አድን ንቅናቄ ለማፍረስ ጥቂት ተከታዮቹን ይዞ ለህወሓት አገዛዝ እጁን የሰጠው የቀድሞው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ሞላ አስግዶም በጠና ታሞ ከሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኝ ተረጋገጠ፡፡
    “ተከተሉኝ ስራ አለ” የሚል ድፍን ያለ መመሪያ ብቻ በመስጠት ይዟቸው ወደ ኢትዮጵያ ሊሻገር ካንቀሳቀሳቸው ታጋዮች አብዛኞቹን በጠይት ካስጨረሰ በኋላ ለጥቂት አምልጦ የህወሓትን ዘረኛ ቡድን መልሶ የተቀላቀለው ሞላ አስገዶም እርስበርሳቸው የሚጋጩ፣ ምንም አይነት መሰረት የሌላቸው ነጭ ውሸቶች በህወሓት መገናኛ ብዙኃንና በየሆቴሉ እየተገኘ ሲናገር ለጥቂት ቀናት ቆይቷል፡፡የሞላ ንግግር እራሱንና አገዛዙን በኢትዮጵያ ህዝብ ትዝብት ውስጥ ጥሏቸው አገር አድን ንቅናቄ የመሰርቱትን የነፃነት ድርጅቶች ሞገስ ከፍ አድርጎ ተቀባይነታቸውን አሳድጓል፡፡
    በህወሓት ርዕዩተ አለም ይሁዳዊነት የተጠመቀው ሞላ አስገዶም ለኢትዮጵያ ህዝብ ፍርድ ከመቅረቡ በፊት በህሊና ፍርድ ተይዞ በገጠመው ድንገተኛ የሆነ ስነ-ልቦናዊና አካላዊ ቀውስ በጠና ታሞ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ውስጥ ተኝቶ ባጣዕር ላይ ይገኛል፡፡

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *