የዘረኛው እና የአምባገነኑ የወያኔ ባለስልጣናት የማስመሰል እና የስለላ ስራውን ሲያከናውን
By Yeruk weldeamanuel
ዛሬ በኦሮሞ ህዝብ ላይ በህዋሀት ቅልብ ወታደር እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ግድያ እና ጭፍጨፋ የሚመሩት ሰዎች ከኦሮሞ ህዝብ ይበልጥ ለልብሱ ከብር ያላቸው ይመስላል።ሆኖም ግን የኦሮሞ ህዝብን በንደዚህ አይነት አስመሳይ ነገሮች አታለን ለዘለአለም ጫንቃህ ላይ ተቀምጠን እንዳሻን እናደርግሀለን የሚባልበት ግዜው አልፎአል ።ዛሬ በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ ገበሬዎች ከመሬታቸው ይፈናቀሉ ሲባል የማንን ኪስ ለማዳለብ እንደሆነ ከናንተ ቅልብ ወታደር ከፊትለፊቱ ቆሞ የሚታገላቹ ገበሬ እንኩዋን ያውቃል።እናንተ እንደምትሉት ለልማት ከሆነ ከመሬቱ ላይ የምታፈናቅሉት ገበሬ ለምን አብሮ የልማቱ ተካፋይ አይሆንም?
ለማኝ ወይም በገዛ መሬቱ ላይ ዘበኛ እንዲሆን ለምን ተፈለገ?እንደእናንተ አስተሳሰብ ከሆነ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በቁጥጥራችሁ ስር አድርጋቹ ሌላውን በባርነት ለመግዛት ይመስላል ።ይህ ደግሞ አሁን ባለንበት ከፍለዘመን ሊታሰብ እንኩዋን የማይችል ነው።በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ የኦሮሞ ገበሬዎች ባለቻቸው መሬት ላይ እያመረቱ እራሳቸውንና ሌላውን ማህረስብ እየመገቡ እንደሚኖሩ ለናንተም ድብቅ አይደለም ታድያ ይህን ምስኪን ገበሬ የት ግባ ነው ምትሉት? ቢቻል በደንብ አምርቶ ለራሱም ለሌላውም እንዲተርፍ የተሻሻለ የግብርና ዘዴ ተጠቃሚ ማድረግ ዛሬ የሱን የባህል ልብስ ለብሶ ህይወቱን ከመንጠቅ ይመረጣል ።
ለማንኛውም ድል ለጭቁን አርሶአደሮች!!!