በስሉልታ ፌደራል ፖሊስ ከወጣቶች ጋር ተፋጧል – የአላሙዲ መኪኖች ተሰባበሩ * ፖሊስ እየተኮሰ ነው

Zehabesha News

(ዘ-ሐበሻ) ከአዲስ አበባው ቤተመንግስት 28.4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሱሉልታ ከተማ የአካባቢው ወጣቶች ከፌደራል ፖሊሶች ጋር በፋጠጣቸው ተሰማ:: ከአካባቢው የሚመጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የሱሉልታ ወጣቶች የኢትዮጵያን ሕዝብ እየገደለ ያለውን የሕወሓት መንግስት በገንዘብ ይደግፋሉ ያላቸውን የሼህ መሀመድ አላሙዲ 3 መኪኖችን በድንጋይ ሰባብሯል::

በሱሉልታ ከተማ የሚገኘ አንድ የኤሌክትሪክ ትራንፎርሜሽን መፈንዳቱን ተከትሎ አካባቢው በፌደራል ፖሊሶች በመከበቡ የተነሳ ሕዝቡ ፖሊሶቹን አትወክሉንም; ከአካባቢያችን ዞር በሉ በሚል ተቃውሞውን ማሰማቱን ተከትሎ ፖሊሶች በወጣቶች ላይ ዱላ ሰንዝረዋል:: አንዳንድ ወታቶችም አጸፋውን በፖሊሶች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ፖሊሶች በተኩስ የወጣቱን ተቃውሞ ለመበተን ሞክረዋል ብለዋል::

ይህ ተቃውሞ እየተደረገ ባለበት ወቅት በአካባቢው ይንቀሳቀሱ የነበሩ የሼህ መሀመድ አላሙዲ ንብረት የሆኑ መኪኖች በድንጋይ ሲደበደቡ የሦስቱም መኪኖች መስታወቶች መርገፋቸው ተሰምቷል::

በሌላ በኩልም በሰበታ የሁለተኛና የፕሪፓራቶሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ወታደሮች እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አስታውቀዋል::

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *