ኢትዮዽያ ኃገራችንን ለህዝብ አሳቢና ሀገር ገንቢ በመምሰል በእርስበርስ ጦርነት ሊያጠፋን የመጣዉን የወያኔ ቡድን ለማስወገድ የትጥቅ ትግል ወሳኝ ነዉ ።

በኢሳ አብድሰመድ    ሀገራችን ኢትዮጵያ ስጋዋ አልቆ በአጥንቱዓ መሄድ ከጀመረች ይኸዉ 25 ኛ ዓመቷን አስቆጠረች  የኃገራችን አምባገነን መሪ እሱ ከሳሽ እሱ ፈራጅ እሱ ዘራፊ እሱ ገዳይ እሱዉ ሀገር ሻጭ እረ ስንቱ ተቆጥሮ ይቻላል ወገኖቼ የኢትዮዽያ አምላክ ይቁጠረው
ወያኔ የታወቀ ነው መቼም ቢሆን ለኢትዮዽያ ህዝብ አይቆምም ቆሞም አያቅም ፡ ታድያ ይህንን ስራውን የተረዱና ያወቁ የአሜሪካንም ሆነ የኤሮፖ አገራቶቾ እርዳታቸውን ግን ሲያቆሙ አላየንም፡ በተጨማሪ በአሁን ወቅት በአገራችን ውስጥ ያለውን ከ 15 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ለርሀብ መጋለጡ የታወቀ ቢሆንም እነዚህው እርዳታ ሰጪ ወይንም ለጋሽ ሃገሮች ስጦታቸውን አላቌረጡም ነገር ግን እርዳታው ለህዝብ ይደርሳል አይደርስም ሌላ ጉዳይ ነው ይህንን ማጣራት የእያንዳንዱ ኢትዮዽያዊ ግዴታና ኃላፊነት ነው ብዬ የማምነው።
ወደ ኪሳቸው እንደሚገባ ብናቅም እንኮአን መከልከል ባንችል የት እንደደረሰ ለዓለም ሚድያ ግን ማሳወቅ ግድ ይለናል በአስተሳሰብ ሳይሆን በሆዳቸውና በጥቅማ ጥቅም የተገዙ አጫፋሪዎች ቢኖሩም እነሱንም ጨምሮ የማጋለጥ ስራ ለመስራት መታገል ነው
እጅጉን የሚሰቀጥጠው እና የሚያሳፍረው በዚህ ወቅት ብዙ ሚሊዮን ብሮችን ግምቦት 20ን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ የኃገሪቱ ክፍሎች የገዥውን አባላቶች ሰብስቦ ዘራፍ ማለቱ የተለመድ ቢሆንም በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች የሚላስ የሚቀመስ ባጡበት ሁኔታ ወገን እንደቅጠል እየረገፈ ባለበት ሰዓት ግንቦት 20ን ማክበር ተገቢ ነው ብዬ አላምንም
እንደምንሰማው ድርቅ ረሃብ ባልተከሰተበት ሁኔታ እዚሁ አፍሪካ ውስጥ ለህዝባቸው አሳቢ የሆኑ መሪዎች የነፃነት ቀን አቸዉን አይከበርም በሚል ወጪው ለሆስፒታሎችና ለተለያዩ መሠረተ ልማቶች እንዲውል ማድረጋቸው ክብርና ውዳሴ የሚያሰጣቸው ሲሆን፡
በተጨማሪ ደግሞ ለሌሎች አምባገነን የአፍሪካ መሪ ትምህርት ሰጪ ይሆናል ብዬ አስባለው ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ   http://www.udakuspecially.com/2015/09/magufuli-afanya-kitu-mbaya.html
ኢትዮዽያ ኃገራችን ጥሩ መሪ ወይንም መንግስት ቢኖራት የዘንድሮ ግንቦት 20 ታስቦ እንዲውል ብቻ በማድረግ በዜጎች ላይ በደረሰው የርሃብን አደጋ ለመታገል ስንል ሰርዘናል ወጪውንም በድርቁ ለተጎዱ ወገኖቻችን እንዲውል አድርገናል ማለት እየተቻለ ጆሮዳባ መባሉም እጅጉን አሳዛኝ ነው ።

ኢትዮጵያዊያንን የማይወክል መንግሥት አዲስ አበባ ላይ ተቀምጧል። ይህ መንግሥት ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነ የፖለቲካ ፍልስፍናና የአስተዳደር መመሪያ አስቀድሞ፤ ሀገራችንን ከአንድነት ወደ ልዩነት በመንዳት፤ ለርስ በርስ ትልቅልቅ እያዘጋጀን ነው። በትውልድ ኢትዮጵያዊ ይሁኑ እንጂ በተግባር ፀረ-ኢትዮጵያዊ ለመሆናቸው መረጃ የሚጠይቀኝ የለም። ግልፅ ነውና! በእርግጥ እስካሁን በተለያዩ ወገኖቻችን መካከል መጠፋፋቱ አልተከሰተም ብዬ አይደለም፤ መጪው መለኪያ የሌለው የከፋ መሆኑን ለመጠቆም ነው። ድህነቱ፣ በበሺታ ማለቁ፣ ያልተመጣጠነ አስተዳደርና እድገት በተለያዩ ቦታዎች መከሰቱና መደልበቱ፣ የአስተዳደር በደል ጣራ መንካቱ፣ የኑሮ ውድነቱ ማሻቀቡ፣ . . . ወዘተ፤ ባጠቃላይ ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ መሄዱ የተዘገበ ነው። ይኼን እንደ አስተዳደር ብልጠት የተሞሽረበት የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ በዕብሪትና ባለው አቅም እየገፋበት ነው።

በተጓዳኝ የተቃዋሚዎቹን ወገን የተመለከትን እንደሆን ደግሞ፤ አንድ ማዕከል የሌለው፣ አንድ የትግል ራዕይ የሌለው፣ እጅግ በጣም የተበታተነ ክፍል እናያለን። በነዚህ የተለያዩ የተቃዋሚ ወገኖች ውስጥ፤ እጅግ በጣም ቆራጥና ሕይወታቸውን ለወገናቸውና ላገራቸው ለመሥጠት ወደ ኃላ የማይሉ ታጋይ ወጣቶች ሞልተውባቸዋል። የአብዛኛዎቹ የነዚህ ወጣቶች ፍላጎት፤ የኢትዮጵያዊያን ነፃነት፣ የሀገራቸው ብልፅግናና እድገት ብቻ ነው። እነዚህ ወጣቶች፤ ማን ነገ በሕዝቡ ተመርጦ መሪ ይሆናል? ማን ይቸነፋል? የሚሉት በአእምሯቸው ቦታ የላቸውም። በመሪዎቻቸው በኩል የተገላቢጦሽ ነው። አሁንም እነኚህ ወጣቶች በአንድነት ለኢትዮጵያ ለመሠለፍ ዝግጁ ናቸው። መሪዎቻቸው ግን አጥር አበጅተውባቸዋል። የነሱ ድርጅት፣ የነሱ ፍልስፍና፣ እነሱ አጥቂና የበላይ ካልሆኑ፤ ትግሉ አፍንጫውን ይላስ ያሉ ይመስላሉ። እናም “ሌሎቹ ስህተተኞች ናቸው”ብለው ይሰብኳቸዋል። ይህ ሊፈርስ የሚችለውና ባንድ ላይ ተሰባስበን ልንታገል የምንችለው፤ የትግሉን ምንነትና መንገድ በአደባባይ ተወያይተንበት ግልፅ ግንዛቤ ስንይዝ ነው።

በኢትዮዽያ ኃገራችን የህዝብ ፍቅር ያለው በህዝብ የተመረጠ መንግሥት ተመሥርቶ ለዜጎች ሁለንተናዊ ችግሮችና መፍትሄዎች ከዜጎች ጋር በጋራ በመተሳሰብ የምንሰራበት ሁኔታ እንዲፈጠር የወያኔ መንግስት ከኢትዮዽያ ውስጥ ከስሩ ተነቅሎ መጥፋት አለበት ብዬ አምናለው ።ይህ ስርዓት ካልጠፋና ከኃገራችን ኢትዬጵያ ካልተወገደ የኃገሪቱዋ እጣ ፋንታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን ሊታሰብበት ይገባል

ኢተዮዽያ ለዘላለም ትኑረ        By Issa Abdusemed

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *