ይህን አሳፋሪ ዜና ይመልከቱ – ሕወሓቶች ማፈር ካቆሙ ሰነባበቱ

በደምቢዶሎ 73 ሚሊዮን ብር የወጣበት የአውሮፕላን ማረፊያ ተመረቀ ይላል ራድዮ ፋና ይዞት የወጣው ዜና:: ዜናው ላይ እንደሚታየው ከአውሮፕላኑ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር እና ወርቅ ነህ ገበየው ይህን አውሮፕላን ማረፊያ ሊመርቁ ሲወርዱ ነው:: በሶሻል ሚዲያ የተሰራጨውና ከታች የምታዩት ፎቶ ግን ኤርፖርቱ ከመሰራቱ በፊት እና ከተሰራ በኋላ ያለውን ሁኔታ ሲያሳይ አይደለም 73 ሚሊዮን ብር 73 ብር የወጣበትም አይመስልም:: ፎቶውን ይመልከቱና ራድዮ ፋና አየር ማረፊያው ተመረቀ ያለበትን ዜና ያንብቡት::

Jock of the day

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ73 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የደምቢ ዶሎ አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ ተመርቋል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙክታር ከደር፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና ሌሎች ባለስልጣናት በተገኙበት ነው አውሮፕላን ማረፊያው የተመረቀው።

ርዕሰ መስተዳደሩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፥ መንግስት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለሚያሳድጉ እና ህብረተሰቡን የበለጠ ተጠቃሚ ለሚያደርጉ ተግባራት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።

በጠጠር ደረጃ የተገነባውን የደንቢ ዶሎ አውሮፕላን ማረፊያ በሚቀጥለው አመት ወደ አስፋልት ደረጃ ለማሳደግ እንደሚሰራም ነው የገለፁት።

የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው፥ ሀገሪቱ በአየር እና በየብስ ትራንስፖርት የተሻለ ስራ እየሰራች እንደሆነ እና በኦሮሚያ በጂማ አባ ጅፋር እና በባሌ ሮቤ ደረጃቸውን የጠበቁ አውሮፕላን ማረፊያዎች መገንባታቸውን ጠቁመዋል።

የነቀምቴ አውሮፕላን ማረፊያም ነገ የመሰረት ድንጋይ ይቀመጥለታል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ስራ አሰፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ዳዊት፥ ኢትዮጵያ 23 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዳሏት ጠቅሰው፥ በቀጣይም ቁጥሩን ወደ 30 ለማሳደግ መታቀዱን አብራርተዋል።

የአውሮፕላን ማረፊያው የሀገር ውስጥ በረራዎችን በተሟላ ደረጃ ለማስኬድ የሚያስችል አደረጃጀት እንዳለውም አስገንዝበዋል።

የደንቢ ዶሎ አውሮፕላን ማረፊያ ቀላል አውሮፕላኖችን የሚያስተናግድ ሲሆን፥ ሁለት ኪሎ ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር ስፋት አለው።

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *