ህወአታዊዉ ኢህአዴግ ጨንቆታል:: ግብፅና ኤርትራ ሽብርን ለመዋጋት የኤርትራ ልማትን ለማፋጠን ወዘተ የሁለትዮሽ ስምምነት አድርገዋል:: የኤርትራዉ ዉጭ ጉዳይና የግብፁ አቻቸዉም ለአንዳች ጉዳይ በአስቸኩዋይ ተገናኝተዋል::

የህወአት አስተዳደር ግብፅ ኤርትራና አግ7ን እየረዳችብኝ ነዉ ብሎ በቅርቡ የሚዲያ መጨቀሚያና ለዚህ ጊዜ ድረስልኝ ሙትልኝ የሚለዉን የማያዉቀዉን የኢትዮጵያን ህዝብ አሁንም የዉጭ ወራሪ አባይ እንዳይገደብ የምትፈልገዉ ግብፅ በኤርትራ በኩል ወራኛለችና ኢትዮጵያዊ የሆንክ ሁሉ ተነስ የሚል ዘለፈንቶ ጥሪ እንደሚያደርግ ይጠረጠራል::

ወያኔ ወደኤርትራ አዲስና በየቦታዉ የተበተነ ጦሩን በህዝብ ስታር አዉቶቡሶች በጎጃም መስመር እያጋዘ ሲሆን አዲስ እግረኛ ጦር ለመመልመል ላወጣዉ ማስታወቂያ ዝር ያለ አለመኖሩ እጅግ ስላስደነገጠዉ ምናልባት ግዳጅ ሊጀምር ይችላል በሚል በመላዋ ኢትዮጵያ ይሞክርና እናሳየዋለን ከዚሁ ከቀናቸዉ ሬሳችን ይወጣል እንጅ ድጋሚ ለዘረኛዉ ህወአት የሚሞት የለም እያለ ነዉ ወጣቱ::
በተመሳሳይ ዜናም ወያኔ ኤርትራ ድንበር ጦሩን የሚቆልለዉና የጦርነት ነጋሪትም የሚጎስመዉ ዋና አላማዉ በአረቦችና በእስራኤል የሚረዳዉን ኤርትራ ለመዉረር ሳይሆን አሰብንም ለማስመለስ ሻቢያንም ለማዉረድ ሳይሆን አቅማቸዉ ያፈረጠመዉን የነፃነት ሀይሎችን ለማጥፋት በመቃዠት መሆኑ የገባቸዉ የነፃነት ሀይሎች እስከአፍንጫቸዉ ታጥቀዉ ከወያኔዉ ህወአታዊ ጦር ጋር ተፋጠዋል::
ህወአት ከነፃነት ሀይሎች ለአገራችን ለህዝባችን ሲሉ በበረሀ የተደራጁትን ነዉ የሚገጥመዉ::
ህዝብ ሆይ ህወአታዊዉ ኢህአዴግ ኢትዮጵያን አይወክልም ስለዚህም ማንም ይሁን ማን ከዘረኛዉ ልንገላገለዉ ከሚገባዉ ህወአት ጋር የሚያደርገዉ ጦርነት ህወአታዊዉ ኢህአዴግ ወደመቀመቅ የሚገባበትን ስልት ነዉ መሸረብ ያለብን:

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *