የሕዝብ እንቅስቃሴ ለማዳፈን በፌስቡክ የሚንቀሳቀሱ አክቲቪስቶችንን አካውንት በማዘጋት ወያኔ ኤኃዲግ ስራ ላይ ተጠምደዋል።

ስለ ነጻነት እታገላለሁ የሚል የትጥቅ ድርጅትም ይሁን የሰላማዊ ተቃዋሚ ድርጅት ስለሃገርና ስለወገን ነጻነት ወሳኝ ትግል ላይ ነኝ ለማለት አንዲት ቃል ብቻ በቂ ናት። ” ቆራጥነት ” ትባላለች
ቆራጥነትን በሃገራችን ብቻ ሳይሆን ከቀደምት የነጻነት ታጋዮች ብንነሳ እነ ቼ ጉቬራና ፡ ፊደል ካስትሮ ሩዝ ኩባን ነጻ ለማውጣት ሲታገሉ የባፕቲስቱታን አምባገነን ሲጥሉ ኩባን ወከሉ በሚሏቸው ኪነታዊም ይሁን ስፖርታዊ ቡድኖች የባፓፕቲስት መንግሥት በሚያደርገው ወከባ ማንም የነጻነት ታጋይ በፍጹም አልተሳተፈም። ቆራጦች ነበሩና።
ሁለት ነገር ወዶ አይሆንምና ከባርነት ለመገላገል ማንኛውንም አምባገነኑ መንግሥት የሚያደርገውን በሃገር ውስጥም ይሁን በውጭ፡ሃገር በፍጹም አብሮ አለመጮህና አለመሳተፍ የነጻነትን ቀን ያቃርባል። ስፖርትና ኪነታዊ ወከባ የሃገራችንን ሕዝብ በተለይም ወጣቱን እንዴት እንደሚያዘናጋ ያስተዋለ ያውቀዋል።
ወያኔዎች ለእኩይ ዓላማቸው ዲያስፖራና ጫካ ሳሉ፡ የዲያስፖራ ሽፍቶቻቸው እነ ሻምበል ምሩጽ ይፍጠርን ከኦሎምፒክም ይሁን ሌላ የአትሌቲክስ ውድድር እንዲከዱ ብዙ ጥረዋል እንጂ በደርግ መንግሥት የኢትዮጵያ ስፖርተኞች ስላሸነፉ ስሜት አልሰጣቸውም። ለነገሩ ወያኔዎች ትግላቸው እንኳንስ ያኔ አሁንም ለታላቋ ትግራይና ለትግራይ ነው።
ሆዳም አጃቢ ባሪያዎቻቸው ተለጣፊዎቻቸውን እነ ኦህዲድ ፤ ብአዴን፤ ደቡብ ምናምን ቅብጥርሶን እርሷቸው፤ ምክንያቱም ሃገራቸው ሆዳቸው ነውና።
አትሌቶቹ በወያኔ አምባገነን ሥር ሆነው ኢትዮጵያን ወከሉ ብሎ አብሮ ወከባ መፍጠር ለወያኔ አምባገነን አገዛዝ የባርነት ሥርአት መንበርከክ ነው። አድማ ማድረግ ሲገባ ልክ ነጻነት ያለ ይመስል ወያኔ የገደላቸው ንጹሃን አስከሬን ሳይደርቅ አብሮ መጯጯህ፤ ማድነቅ ምንድነው? አትሌቶቹ የሮጡበትና 1ኛ የወጡበት ሩጫ ነጻነት አይሆን ነገር። ነጻነት ያላቸው ሃገሮች ቢጮሁና ቢንዘላዘሉ ያምርባቸዋል። ነጻነት የሌለው ሕዝብ በስፖርት ወከባ ጥርሱን ቢያሳይ ልቡ የደማና ግራ የገባው ባይተዋር ነው።
አትሌቶቹ ድል ባገኙ ቁጥር በዓለም መንግሥታት ወያኔ ይወደሳል፤ በጠመንጃ ጥይት የሚገደለው የምስኪኑ ደምና ሕይወት በዜና ተነገሮ ብቻ ዝም ብቻ ሳይሆን፡ በሃገር ውስጥ ያለው ሕዝባችንም ሥነልቡናው ተሰልቦ እኅኅ እያለ ለፈጣሪው አምላኩ በጸሎት ነግሮ ዝም ነው።
አምላክችን ግን ከእንሥሳት ለይቶ እንድናስተውል አእምሮ ሰጥቶናል። በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ እንደተጻፈው ንጉሥ ዳዊት ነቢይ ስለሆነ በትንቢት አልነበረም እሥራኤላውያን ከፍልስጠኤም የባርነት አገዛዝ ነጻ ያወጣቸው። በመዝሙረ ዳዊት ላይ የተጻፈው ጸሎቱ ላይ ተዋጊ ወታደር እነደነበርና ጠላቶቹን የተቁቋመው ተንቀሳቅሶና ተዋግቶ ቢሆንም በጸሎቱን ላይ እግዚአብሔርን ኃይል ስጠኝ እያለ እንደነበር ተጽፎ አንብበናል።
3ቱን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ወደላይ ከፍ አድርገን የምናውለበልበው ሃገራችንን ከገደላት ከፋሽስት ወያኔ ሕወሃት ጋር አይደለም!!! ከነጻነታችን ጋር ብቻ!!!!!! ” ድንበሯና ሕዝቧ የተከበረ ሃገር ሲኖረን ነው በኦሎምፒክ አደባባይ ሆይ ሆይ ማለት የሚገባን።

“በፋሽስት ወያኔ አምባገነን ሥር ሕዝቦቿ የምትሰቃየው ሃገሬ መላውን የኦሎምፒክ ውድድር በወርቅ ሜዳሊያ ብታሸንፍ በኔ በኩል ቅንጣት ታህል አልደሰትም። ለእኔ የወርቅ ሜዳሊያዬ የሕዝባችን ነጻነት ብቻ ነው።”

—የወያኔን ፋሽስት አምባገነን የትግሬውን ሕወሃት ቡድንም የምናሸንፈው ኢትዮጵያን በመንግሥትነት ወክያለሁ ብሎ በሚያዘጋጀው የዓለም አቀፍ ስፖርትም ይሁን የሃገር ውስጥ ኪነታዊም ይሁን የስፖርት ወከባ ላይ በመካፈል ሳይሆን በአድማና በትጥቅ ኃይል ብቻ ነው።
ስፖርቱን ብቻ ሳይሆን ወያኔ የሚመራውን ማንኛውንም ዓለም አቀፍ ተሳትፎ አብሮ ባለማጨብጨብ ፤ አብሮ ባለመጨፈር ማሳበድ ነው። ያኔ ታዲያ የጠፋው ትውልድ ከተኛበት እንቅልፍ ” ቆራጥነት ” ወደምትባለው ትግል ያመራል።

ሞት ለፋሽስት ወያኔ !!!

ኢትዮጵያ ትቅደም!!

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *