ዘረኛው እና አምባገነኑ የወያኔ ቡድን ያመጣብን የመንጋ ፓለቲካ መጨረሻው ጥፋት ነው፦

ወያኔ የብሄር(የመንጋ) ፓለቲካ አምጥቶ ከጫነብን ጊዜ አንስቶ ለዘመናት ያካበትናቸውን አገራዊ የጋራ እሴቶች እየተሸረሸሩ እጅግ የጦዘ የመንጋ ፓለቲካችንን እያከረርነው ወደ ማጡ እንድንነጉድ አድርጎናል።

የመንጋ ፓለቲካ በቋንቋ ማንነት ላይ ብቻ በመሰባሰብ አያበቃም። ሌሎች ማንነቶች ለምሳሌ ጎሳ፣ሃይማኖት፣በመንደር ሳይቀር ይገበል። በሰወች ልዬነት ላይ የሚያጠነጥን ፓለቲካ መጨረሻው ጎልተው ያልወጡ ልዬነቶች በመብራት እየተፈለጉ የመንጋን ፓለቲካ ማቡካቱ ይቀጥላል። ዛሬ ላይ ደቡብ ላይ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ተብሎ የአንድ መንጋ ስብስብ ይምሰሉ እንጂ ጊዜው ሲደርስ የምናየው የሰፋ መንጋወች ብቅ ብቅ ማለት ይጀምራሉ። ለምሳሌ የወላይታው እና የሲዳማው ክለቦች እግር ኳስ ሲጫወቱ የፌደራል ፓሊስ ቁሞ እየጠበቀ ነው። ወያኔ የቀበራቸው በርካታ ጊዚያቸውን ጠብቀው የሚፈነዱ መንጋወች ቤት ይቁጠረው።

በኦሮሚያ ክልልም ቢሆን ያው ነው። ዛሬ ላይ የመንጋው ፓለቲካ በቋንቋ አንድነት ላይ ያነጣጠር መሰባሰብን ልናይ እንችላለን። ነገር ግን የወለጋው ከአርሲው፣ አርሲው ከባሌው፣ ቦረናው ከሌላው፣ ሸዋው በርካታ የሃይማኖት፣የጎጥ እና መሰል ልዮነቶች እየተሰነጠቁ መንጋወች መብዛታቸው አይቀሬ ነው።

በሌላውም ብሄር ላይ ችግሩ ተመሳሳይ ነው። በሃይል ተይዞ እንጂ ከፋብሪካ እንደወጣ ሳሙና አንድ ቁም የሚመስሉን የትግራይ ሰወች በውስጣቸው ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዱ ልዮነቶች ሞልተዋል። አብዛኛው የትግራይ ህዝብ አደዋውን የሚያይበት መነፀር የተለየ ነው።

ብቻ ምንአለፋቹህ በልዮነት ላይ ያተኮረ የመንጋ ፓለቲካ መጨረሻው ተያይዞ መጥፋት ነው።

የአለም የ21ኛው ክፉለዘመን አስተሳሰብ በእውቀት ላይ የተመረኮዘ ማህብረሰብ ነው። እውቀት ከየትኛውም ጠርዝ ይምጣ በየትኛውም ቦታ ላይ ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል። ዘሙኑ የዋጀው አስተሳሰብ ድንበር የለሽ የግለሰብን ነፃነት ላይ ትኩረት ያደረገ የህዝቦች ባህላዊ፣ሃይማኖታዊ እና ማንነታዊ ልዮነቶች የአለማችን ውበቶች እና ጌጦች እንጂ የመተላለቂያ የመንጋ ፓለቲካ ሰለባወች አይደሉም።

ለሁሉም አዋጪው መንገድ ዜጎች ሁሉ የተከበሩባት ዲሞክራሲያዊት አትዮጵያን ስንመሰርት ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ያለው መንገድ ሁሉ በአንክሮ ለተመለከተው የጨለማ መንገድ ነው።

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *