የቤንሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ በአንባገነኑ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት አደረሰ

 

የቤንሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ በአንባገነኑ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት አድርሷል በታህሳስ ወር ተከታታይ ቀናት ወያኔ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ብሎ በሚጠራው አካባቢ ጋማድ በተባለ ልዩ ቦታ የቤንሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ በህወሓት መሳሪያ አንጋቾች ላይ በከፈቱት ድንገተኛ ጥቃት 13 የወያኔ ሰራዊቶች ሲገደሉ ከ8 በላይ የቆሰሉ ሲሆን በርካታ የነፍሶከፍና የቡድን መሳሪያ መማረካቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በዚሁ በቤንሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ክልል በሱዳን ድንበር አካባቢ ልዩ ቦታው መኩዋር ሹሩ ቆሌ በተባለ ስፍራ በዚሁ ታህሳስ 23
ቀን 2009 ዓ.ም. የቤንሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄና በአገዛዙ ታጣቂዎች መካከል በተደረገ ከፍተኛ ውጊያ ከ40 በላይ የህወሓት ስራ አስፈፃሚ እና የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፖሊሶች ሲገደሉ ከ80 በላይ ደግሞ ቁስለኛ በመሆን አሶሳ ከተማ የሚገኘውን ራሻ ሆስፒታል አጥለቅልቀውታል ከዚሁ ጋር በተያያዘ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ለነፃነት ታጋዮች ስንቅና ውሃ አቀብላችኋል በማለት በበርካታ ዜጎች ላይ ድብደባና እስር እንደፈፀመባቸው ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ፡፡

Relatert bilde

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *