በባህርዳር ከተማ የህወሃት አባላት ጥቃት ደረሰባቸው

 

የህወሃት አባላቱ  አናፋችሁ አናፋችሁ አሁን ጸጥ አላችሁ ድሮም ከእኛ አታመልጡም እያሉ ሲዝቱ እንደነበር የሚገልጹት ምንጮች በከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የነበሩት የአካባቢው ወጣቶች ከእያካባቢው በመሰባሰብ በጠርሙስና በቦክስ ድብደባ ፈጽመዋል። ተደብዳቢዎቹ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ወደ ሆስፒታል በአምቡላስ ተጭነው ተወስደዋል። ጥቃቱን የፈጸሙት ወጣቶች አንዳቸውም አልተያዙም።

ድርጊቱ ሆን ተብሎ ጸብ ለመፍጠር የተቀነባበረ እንደሆነ ምንጮች ይገልጻሉ። የህወሃት አባላቱ በተለያዩ ሆቴሎች እየገቡ በመጠጣት የትንኮሳ ቃላትን ይናገሩ ነበር።

ዳሸን ቢራ እንዳይጠጣ ህዝብ ማእቀብ በጣለበት ወቅት ዳሸን ቢራ ሆን ብለው መጠጣታቸው እንዲሁም  ወጣቶችን ታናፋላችሁ ብለው አስጸያፊ በሆነ ቃላት መሳደባቸው እና የክልሉን ህዝባዊ ተቃውሞ እንደተቆጣጠሩት መናገራቸው በሁለቱ ህዝቦች መካከል ሆን ብለው አለመተማመን እንዲኖርና ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ ህወሃት ያቀናበረው ሴራ ነው በማለት ምንጮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

እንዲህ አይነት ተንኮሳዎች በተከታታይ ሊኖሩ እንደሚችሉም ምንጮች አስጠንቅቀዋል።በባህርዳር ከተማ ባለፉት ሁለት ቀናት ከፍተኛ ፍትሻ ሲደረግ ቆይቷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዳሽን ቢራ አናወርድም የሚሉ ሆቴሎች ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ታውቋል። የክልሉ ህዝብ የህወሃት እና ብአዴን የጋራ ንብረት የሆነውን ዳሸን ቢራን መጠቀም በማቆሙ፣ ሆቴሎችም ላይሸጥልን አናወርድም እያሉ ነው።

ይሁን እንጅ ዳሸን አናወርድም በሚሉት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድባቸውና ሆቴላቸውም እንደሚታሸግባቸው እንደተነገራቸው አንዳንድ የሆቴል ባለቤቶች ለኢሳት ዘጋቢ ተናግረዋል። በርካታ ሆቴሎች ዳሽን ቢራን በፍሪጅ ለማስቀመጥ በመቸገራቸው አውጥተው ለመድፋት እየተገደዱ ነው።

news abbaymedia.com

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *