በቃሊቲ እስር ቤት ባሉ የፓለቲካ እስረኞች ላይ ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተነገረ | አባይ ሚዲያ

አባይ ሚዲያ ዜና  ወንድወሰን ተክሉ
በአዲስ አበባ ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ባሉት የህሊና እና የፖለቲካ እስረኞች ላይ አግባብነት የሌለው ከፍተኛ የሆነ አካላዊ
ጥቃት እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ከስፍራው ካገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
ለእስረኞቹ አካላዊ ጥቃትና ስቃይ በእስር ቤቱ ጠባቂዎችና አመራሮች እንዲደርስባቸው ምክንያት የሆነው በውሃ ቀጠነ ህግ
አሳሪዎቹ የታሳሪዎቹን ሞራል፣ ስነ-ልቦና እና መንፈሳቸውን ለመስበር ሆን ብለው እያደረጉት እንደሆነ ነው ከስፍራው
የደረሰን መረጃ የሚገልጸው። የፖለቲካ እስረኞችን በተናጠል ኢላማ ያደረገው ይህ የእስር ቤቱ ጥቃት በቃሊቲው ስድስተኛ
ፍርድ ክልል፣ ዞን አራት በሚባሉት እነ ዶ/ር መረራ ጉዲና ባሉበት ክልል እንደሚበረታ ተገልጿል።
የፖለቲካ እስረኞቹን በጨለማ ቤት በመዝጋት፣ ከቤተሰብ ጋር እንዳይገናኙ በማድረግ፣ በሲሚንቶ ወለል ላይ እንዲተኙ
በማድረግና በአካላዊ ድብደባ እንዲፈጸምባቸው በማድረግ ጠባቂዎቹ እስረኞቹን በማሰቃየት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
በአዲስ አበባ ማእካላዊ እስር ቤት ውስጥ ጉዳያቸው በምርመራ ላይ ባሉ ተጠርጣሪ የፖለቲካ እስረኞች ላይ ዘግናኝ የሆነ
ኢ-ሰብዓዊ ምርመራዎች እንደሚፈጸም እንደ እስረኛ ሀብታሙ አያሌው አይነቶቹ እንዳጋለጡ ይታወቃል።
ሆኖም የቃሊቲ እስር ቤት ይዘት ጉዳዩ የምርመራ ስራ ያበቃለት ተጠርጣሪ እስረኛ እና የተፈረደበት እስረኛ መቆያ ሆኖ ሳለ
ለምን በእስር ቤቱ ጠባቂዎች፣ አስተዳደሮችና የበላይ ሃላፊዎች እስረኞቹ አካላዊ ጥቃት እንዲፈጸምባቸው እንደተደረገ
ብዙዎቹን እንዳሳዘነ መረዳት ተችሏል።
የቃሊቲው እስር ቤት ውስጥ ያሉትን የፖለቲካ እስረኞች እንደነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ አቶ በቀለ ገርባ፣
አቶ አንዱዓለም አራጌ…ወዘተ የመሳሰሉ ቁጥራቸው በሺህ የሚቆጠሩ ያሉበት እስር ቤት ሲሆን፣ እስረኞቹም ከትግራይ
በመጡ የአንድ ብሄር ነገድ ታጣቂዎች ተከበው እንደሚጠበቁና በእነዚሁም ጠባቂዎቻቸው እየተጠቁ እንደሆነ ነው ለማወቅ
የተቻለው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ያመጧት በወጣጧ ንግስት ይርጋ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ከአካባቢዋ
ማግኘት ባለመቻሉ የሀሰት ምስክር እንዳዘጋጀባት ለመረዳት ተችሏል።
ወጣት ንግስት ይርጋ ባለፈው ዓመት በአማራው ክልል በተነሳው ህዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ተይዛ ወደ አዲስ አበባ
ማእከላዊ የተወሰደች ሲሆን እሷ በተከሰሰችበት የክስ ፋይል ሌሎችም በአባሪነት ተካተው በቃሊቲ እንደታሰሩ ይታወቃል።

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *