አመፁ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች እየሰፋ መሆኑ ታወቀ

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ሞጣ ከተማ የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ጀምሯል በርካታ የሞጣ ነጋዴዎች ሱቃቸውን በመዝጋት ተቃሟቸውንና የትግሉ አካል መሆናቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡
በኦሮሚያ ሻምቡ ከተማ አድማው እንደቀጠለ ሲሁን በወልቂጤና በበርካታ ከተሞች የስራ ማቆም አድማው አድማሱን እያሰፋ እየቀጠለ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በአዲስ አበባ በሚገኘው በመርካቶ ገበያ ማዕከል ተቃውሞ በመነሳቱ፤ በርከት ያሉ የንግድ ቤቶች ዝግ ኾነው ውለዋል። የጣና ገበያ አዳራሽም በመዘጋቱ ምክንያት መርካቶ ጭርና ቅዝቅዝ ብላ አርፍዳለች።
መንግሥትን የሚወክሉ ካድሬዎችና ፖሊሶች በአካባቢው በመዘዋወር ንግድ ቤቶቹን አስገድደው ለማስከፈት ሙከራ ቢያደርጉም፤ እስካሁን የተሳካ ውጤት እንዳልተገኘ ታውቋል።
ተቃውሞው እስካሁን ካንዱ ከተማ ወደ አንዱ ከተማ እየተዛመተ ሄዶ፤ አዲስ አበባ ቢደርስም ተቃውሞውን ለማብረድ መንግሥት የኃይል እርምጃ ከመውሰድ በቀር የወሰደው መፍትሄ ስለሌለ፤ ኹኔታው ሊባባስ እንደሚችልና ከፍተኛ የሕዝብ አመጽም ሊቀሰቅስ እንደሚችል ብዙዎች ይናገራሉ።
በሌላ ዜና ፡- የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ በመጠየቅ በፋብሪካው ቅጥር ጊቢ ውስጥ ሰልፍ አደረጉ፡፡ የደሞዝ ጭማሪ የማይደረግላቸው ከሆነ አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ሰራተኞቹ የሚከፈላቸው ደሞዝ አነስተኛ በመሆኑ ህይወታቸውን በአግባቡ ለመምራት እንደተቸገሩ ይገልጻሉ

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *