የባህርዳር ከተማ በከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ ውስጥ ትገኛለች!

ዛሬ ነሀሴ 3 ቀን 2009 ዓ/ ም ከረፋድ 5:00 ጀምሮ ቁጥራቸው እጅግ በርካታ የሆነ የፀጥታ ኃይሎች በባህርዳር ከተማ ተሰማርተዋል፣ ሙሉ በሙሉ የመንግስት ተቋማት፣ ባንኮች፣ ፖሊስ ጣቢያዎች፣ የመንግስት ቢሮዎች እንዲሁም ህዝቡ ቀደም ሲል የሹማምንቱ ድርጅቶች እንደሆኑ የሚጠረጥራቸው እንደ ግራንድ፣ ኩሩፍቲ፣ ሆምላንድ ሆቴል፣ አቫንቲ፣ ፓፒረስ ሆቴል ወዘተ በጥበቃ ላይ መሆናቸው ታውቋል፣ እንዲሁም በከተማዋ በየ 3 ሜትር እርቀት ሙሉ ትጥቅ የታጠቁ ወታደሮች በተጠንቀቅ በመቆም ያነገቱትን መሳሪያ አውርደው እና ወድረው ይገኛሉ። ህብረተሰቡ ምን ሁነው ነው? ምን ገብቶ ነው በከተማው? ወዘተ እያለ በአንክሮ እየተመለከታቸው ሲሆን አንዳንድ የፀጥታ ኃይሎች ከየት እንደመጡ አይታወቅም ግራ ተጋብተው ይታያሉ ከሌላ ቦታ እደመጡ ይታወቅባቸዋል። በመሆኑም ወያኔ ከሌላ ቦታ ያመጣቸውን ወታደሮች በከተማው ውስጥ የአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች ገብተዋል ተብሎ እደተነገራቸውና ከተማዋን ሊያናውጣት ነው ተብለው እደመጡ በመናገር ላይ ይገኛሉ አሁን ግን በቦታው መጥተው ያዩትና የተነገራቸው የተለያየ መሆኑን ተገንዝበዋል። ቀደም ሲል እደተናገርነው እናንተ የፀጥታ ሰዎች ለማን ነው የቆምነው ለህዝብ ወይስ ለጨቋኞች? ህዝቡ ምኑን ነው እየጠየቀ ያለው የፍትህ፣ የዴሞክራሲ፣ የነፃነት ነው እየጠየቀ ያለውም እናንተ የፀጥታ ኃይሎች ነፃ እድትወጡ ነው!! በመሆኑም እናንተን ከህዝባቹህ ጋር እድትጋጩ የራሳቹሁን እናት፣ አባት፣ እህት፣ ወንድም እደምትገድሉ ስትላኩ ገዥዎች ግን በሞቀ ቤታቸው ጮማ እየቆረጡ፣ ውስኪ እየተራጩ፣ ልጆቻቸውን እና ዘመዶቻቸውን በአገሪቱ ሃብት አደፈለጉ እየሆኑ ነው፣ ስለዚህ ቆም ብላቹሁ የምታስቡበት ጊዜው አሁን ነው እንላለን። ድል ለኢትዮጲያ ለህዝብ!!! 


You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *