በሜክሲኮ 116 ሰዎች በመሬት መንቀጥቀጥ ተገደሉ | አባይ ሚዲያ

በወንድወሰን ተክሉ
ከሜክሲኮ ከተማ 120 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ በተፈጠረ የመሬት መንቀጥቀጥ እስከ አሁን የ116 ሰዎች ህይወት መጥፋቱ የተገለጸ ሲሆን የማቾቹ
ቁጥር ይጨምራል ሲል መንግስት መግለጹ ታውቋል።
የ1985ቱን አሰቃቂና 8.1 ማግኒቲዩድ ርህደ መሬት ጥቃት በማስታወስ ዋዜማ ላይ ያለችው ሜክሲኮ ከዋና ከተማዋ 120 ኪሎ ሜትር እርቀት
ላይ የተከሰተው የዛሬው ርህደ መሬት 7.1 ማግኒቲዩድ ሃይል ያለው ጠንካራና ሃይለኛ ሲሆን በዋና ከተማዋ ሜክሲኮ በደርዘን የሚቆጠሩ ህንጻዎችን
በማውደም የ116 ሰዎችን ህይወት በመቅጠፍና ወደ አራት ሚሊዮን የሚጠጉትን ደግሞ ቤት አልባ እንዳደረገ ለማወቅ ተችሏል።
የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አስቸካይ ስብሰባ በመጥራት የነፍስ አድን ዘመቻን ያወጁ ሲሆን መከላከያ ሰራዊቱን በማሳመራት በፍርስራሽ ስር ያሉትን ነፍስ
የማዳንን ተግባር እያስፈጸሙ እንዳሉ ተገልጿል።
በሃይለኝነቱ 7.1 ማግኒቲዩድ ያስመዘገበው ርህደ መሬት 53 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ጥልቅ ጉድጓድ በተነሳበት ዋና ስፍራ መፍጠር መቻሉም
አብሮ ተገልጿል

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *