ከመከላኪያና ከፖሊስ ሠራዊት አባልነት ለመሰናበት ማመልከቻ የሚያስገቡ አባላት ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ለህወሃት ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮበታል ተባለ

በህወሃት የበላይነት የሚመራው አገዛዝ የሥልጣን ዕድሜውን ለማራዘም በህዝባችን ላይ የሚወስደው ፋሽስታዊ እርምጃ እረፍት የነሳቸውና የገዛ
ወገናቸውን ማሰርና መግደል ወንጀል መሆኑን እየተረዱ የመጡ የአገር መከላኪያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት የሥራ መልቀቂያ በብዛት ማስገባት
መቀጠላቸውን ቅርበት ካላቸው ምንጮች ለማወቅ ተችሏል።
የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባት ላይ ያሉ የፖሊስና የመከላከያ አባላት ከተራ ወታደር እስከ ከፍተኛ ባለማዕረግ ያሉ እንደሆኑም ከምንጮች የተገኘው
መረጃ ያመለክታል።
ቀደም ሲል የመልቀቂያ ጥያቄ በማቅረብ ይታወቁ ከነበሩት የአዲስ አበባ ፖሊሶች በተጨማሪ በአማራና በኦሮሞ ክልሎች የሚገኙ የፖሊስ አባላትም
በብዛት የስንብት ደብዳቤ ማቅረብ መጀመራቸው አገዛዙ ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮአል ያሉ ምንጮች የመከላኪያ ሠራዊት አባላትም ከያሉበት ክፍለ
ጦር በብዛት ስንብት እየጠየቁ ናቸው ብለዋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አባል የሆነና አሁን በሥራ ላይ ያለውን ኮሚሽነር ይተካል ተብሎ ከፍተኛ አመኔታ የተጣለበት ኮማንደር ደረጃ
አቻምየለህም እንዲሁ ሥራውን ለመልቀቅ ሰሞኑን የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባቱ ታውቋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ሰሞኑን አገር ውስጥ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ የገዛ ህዝባችን ላይ አንተኩስም በማለት ተቃውሞ ያሰሙ ፖሊሶች ቁጥር
እየተበራከተ መምጣቱ አገዛዙን ክፉኛ እንዳሳሰበው ይነገራል። በትናንትናው የትንሳኤ ሬዲዮ ዜና ዘገባ የነቀምት ፖሊሶች ለተቃውሞ በወጣው ህዝብ
ላይ አንተኩስም በማለት ከመከላኪያ ጋር ተፋጠው እንደዋሉ የተገለጸ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከሃረር ከተማ ፖሊስ ምንጮች በደረሰን ዜና ደግሞ
የሃረርና የዲሬደዋ ፖሊሶች ተመሳሳይ አቋም መያዛቸው ታውቆአል።
ሻሸመኔ ላይ ከትናንት በስቲያ ተደርጎ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ የክልሉ ፖሊስ ከህዝብ ጋር በመወገን የ6 ንጹሃን ዜጎችን ደም ባፈሰሱ የአጋዚ ጦር
ላይ እርምጃ ለመውሰድ ተንቀሳቅሶ እንደነበር መዘገቡ ይታወሳል። አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ህዝባዊ ተቃውሞ ቢቀሰቀስ ፖሊስ ከአገዛዙ ጋር ወግኖ
እንደማይቆም ወያኔ መረጃ እንዳሰባሰበ የሚናገሩ የፖሊስ ምንጮች አሉ።

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *