የኬኒያው ተቃዋሚ መሪ ሀገራዊ እምቢተኝነት ንቅናቄ ማቋቋማቸውን ይፋ አደረጉ

የኬኒያ ተቃዋሚዎች ጥምረት ናሳ [National Supper Alliance/NASA]  ረቡእ አመሻሹ ላይ ባደረገው ድንገተኛ መግለጫ ድርጅቱ ነገ በሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ እንደማይሳተፍ ለመጨረሻ ግዜ ይፋ ካደረገ በኋላ
ከአሁን በኋላ ከናሳነት ወደ ብሔራዊ እምቢተኝነት ንቅናቄ [National Resistance Movement/NRM] ተለውጧል ሲሉ የድርጅቱ ሊ/
ርና እጩ ፕሬዚዳንት አቶ ራይላ አሞሎ ኦዲንጋ ይፋ አደረጉ።
በሌላ በኩል ደግሞ ባለቀ ሰዓት ምርጫው እንዳይካሄድ ወደ ጠ/ይ ፍርድ ቤት አቤቱታ አስገብቶ በነበረው የተቃዋሚው ናሳ ጉዳይ ላይ ፍርድ
ለመስጠት ችሎት ተሰይሞ የነበረ ቢሆንም በዳኞች አለመሟላት ምክንያት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለማስተላለፍ እንዳልቻለ መግለጹም ታወቀ።
የጠ/ፍ/ቤቱ ሂደት የነገውን ሀገር አቀፍ ምርጫ እንዳይካሄድ ማገጃ የመስጠት የመጨረሻ እድል ነበር ሲሉ ተንታኞች ይናገራሉ።
ገዢው የኢዩቤልዩ ፓርቲ ምርጫው ያለተቃዋሚው ተሳትፎ መካሄድ አለበት በሚለው አቋሙ በመጽናት ነገ በብቸኝነትና ያለምንም ተፎካካሪ
ምርጫውን ያካሂዳል ተብሎ ተገምቷል።
ሀገሪቷ ወደ አለመረጋጋት እየሄደች ነው የሚለውን የዲፕሎማቶችና የልዩ ልዩ ህብረተሰብ ክፍሎችን ስጋት እውን ያደረገው የተቃዋሚው የብሔራዊ
እምቢተኝነት ንቅናቄ መመስረት ያጠናከረው ሲሆን ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ከምርጫው ማግስት ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ይቀጣጠላል ሲሉ አቶ
ራይላ ኦዲንጋ ተናግረዋል።
እንደ አቶ ራይላ ኦዲንጋ ከሆነ ከነገ በስቲያ ጀምሮ ንቅናቄው የተለያዩ የመታገያ ስልትና ታክቲኮችን በመጠቀም ለመብታቸው እንደሚታገሉ የገለጹ
ሲሆን ኢኮኖሚ ላይ ያነጠጠረው ኢላማቸውም አንዱና ዋነኛው ክፍል ነው ብለዋል።

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *