ሰበር_ዜና  በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ዳግም ውጥረት ውስጥ ገባ !

ጥቅምት  27 ቀን 2010 ዓ/ም የስርዓቱ አመራሮች የጠሩት ስብሰባ በህዝቡ እና በወያኔ መካከል በተፈጠረ ፍጥጫና
ሁውከት ሊቃረጥ ችላል ሰብሳቢዎችም በህዝቡ ቁጣ ደንግጠው አዳራሹን በፍጥነት ለቀው ሲወጡ ታይተዋል ፡፡
የዚህ ስብሰባ ዓላማ የጭልጋ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን አይከል በማን ስረሸ ትሆን ? በነበረችበት ትቀጥል ወይስ
በአዲስ መልክ ለሚደራጀው የቅማንት አስተዳደር ትሁን በሚለው ዙሪያ ለመወያየት ለጥቅምት 19 ቀን 2010ዓ/ም
ተቀጥሮ በህዝቡ ቁጣና እምቢተኝነት ሳይኪሄድ በመቅረቱና “ራሳቸውን የቅማንት ኮሚቴ” ብለው የሰየሙ ሰዎች
አቢቱታ በማቅረባቸውና ህወሓትም ግፌት ተጨምሮበት ለጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ/ም እዲካሔድ መመሪያ ለሰሜን
ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ በአሁኑ አጠራር የማዐከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ ለሆነው ለአየልኝ መመሪያ ተሰጥቶት እሱም
ራሱ እና የዞኑ የብአዴን ኃላፊ ዩሀንስ የተባለውን እና ምክትል አስተዳዳሪ የሆነውን አላምረው የተባለውን በመያዝ
በትናንትናው ቀን በከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃና አጀብ ከረፋድ 4:00 አይከል ከተማ ደረሱ እነሱ ወደ መሰብሰቢያ አዳራሹ
በጋሮ በኩል ሲገቡ በአዳራሹ መግቢያ በር ላይ ወደ አዳራሹ እንገባለን አትገቡም በሚል ጭቅጭቅ ፍጥጫ ነበር በር
ላይ ያሉ ፈታሽ ፖሊሶች የጥሪ ወረቀት አላዛቹሁም አትገቡም ሲሉ ወደ ስብሰባው የመጡ ደግሞ ይሄ እኮ ድግስ
አይደለም የአገር ጉዳይ ነው ሰው ተለይቶ የሚጠራበት አይደለም የቀበሌው ነዋሪ መሆን ብቻ በቂ ነው መታወቂያችን
እየታየ ልንገባ ይገባል በማለት ጥሰው የገቡ ነበሩ ፡፡ ከዚያም ስብሰባው ከተቀመጠለት ሳዓት ዘግይቶ ከ1ሳዓት በኃላ
ተጀመረ ፡ አየልኝ ስብሰባው ለምን እደተጠራና ምን መሆን እዳለበት መድረኩን እደከፈተ አንድ ግለሰብ የቅማንት
ተወላጅና ራሱን የኮሚቴው አባል ያደረገ በስብሰባው ላይ በተገኙ የእስልምና እምነት ተከታዬች ላይ “እነዚህ
ሞስሊሞች ለምንድን ነው ወደ ስብሰባው የተጠሩት እነዚህ እኮ እስላም መጠሪያቸው ሲሆን ብሔር ግን የላቸውም
በመሆኑም ከስብሰባው ሊወጡ ይገባል ” በማለት ሲናገር አዳራሹ በተቃውሞ ተናወጠ የተለያዩ አስተያየቶችና
ስድቦች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲሰነዘሩ መድረክ መሪዎች ተሰብሳቢውን ማረጋጋት አልቻሉም ተሰብሳቢውም እነዚህን
አመራሮች “የህወሓት ተላላኪዎች ፡ ባንዳዎች ፡ እስከመቼ ነው እንደዚህ የምትሆኑት ከኦሮሚያ አመራሮች አትማሩም
ወዘተ ” የሚሉ ስድቦች ሲወርድባቸው ሀሳቡን እና ቁጣውን መቋቋም ሲያቅጣቸው በጋሮ በኩል ሾልከው ወጥተዋል
ስብሰባው ተለዋጭ የቀን ቀጠሮ ሳይሰጠው በህዝቡ እቢተኝነት ተበትናል ፡ ከዚያም ተቃውሞው እና የህዝቡ ቁጣ ወደ
ሁውከት እና በኃይል የተደገፈ ተቃውሞ ይቀየራል ብሎ የሰጋው ወያኔ በርካታ ወታደሮችን እስከ አየር መቃወሚያ
መሳሪያ የያዙ ወታደሮችን አስገብቶ ሙሉ በሙሉ በከተማው ያሰማራ ሲሆን በከተማውና በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት
ነግሳል የአግ 7 ታጋዬችም በዙሪያው ታይተዋል ተብሎ በርካታ ኪላዎች ተቋቁመው ፍተሻ እየተደረገ ነው አንዳንድ
የስርዓቱ የካብኔ አባላት ሀብታቸውን እና ቢተሰቦቻቸውን ወደ ጎንደር እያሸሹና የተወሰኑ አመራሮችም ከተማውን ለቀው
እየወጡ ይገኛል ፡፡ አቶ አየልኝ የዞኑ አስተዳዳሪ በተለያዩ የመገናኛ ቡዙሀን በተለይም በሪፖርተር ፡በኢቢሲ ፡ በፋና
እየቀረቡ ስለ ሰላም እና መረጋጋት ፡ እንዲሁም መሉ በሙሉ ባይክድም በዞኑ በአንዳንድ ቦታዎች የአግ7 ታጋዬች
እንቅስቃሴ መኖሩን በመግለፅ ዞናችን ፍፁም ሰላም ነው እዲያውም በቅርቡ በዞናችን የተለያዩ ስብሰባዎችና በተለይም
የትግራይ ህዝብና በአማራ ህዝብ መሀከል የሰላም ኮንፈረስ ይደረጋል እያሉ ሲሰብኩ ባሉበት ወቅት እንዲህ አይነቱን
የህዝብ መድረክ ማረጋጋትና በተቆጣ ህዝብ ፌት መቆም አስደንግጣቸው እሩጠው ወጥተዋል ፡፡ በመሆኑም በአሁኑ
ሳዓት በዞኑ ከፍተኛ ውጥረት የነገሰ ሲሆን በጎንደር ከተማም የፋሲል እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች አዲግራት ላይ
ከፍተኛ ድብደባ የተፈፀመባቸው ሲሆን ይሄ ደግሞ በከተማው ነዋሪዎች ቁጣን ቀስቅሷል አንድም የወያኔ አመራሮች
ይሄን አፀያፊ ድርጊት አውግዘው መግለጫ አለመስጠታቸው በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሪታን ፈጥራል ፡፡ በመሆኑም
ህዝባችን በአሁኑ ሳዓት በስርዓቱ ተስፋ የቆረጡ ሲሆን ከነፃነት ታጋዬች ጋር በርካቶች እየተቀላቀሉ እና ጥያቂ እያቀረቡ
ይገኛሉ ፡ ስለዚህ ለነፃነታችን ስንል ትግላችንን እድናደርግና ስርዓቱን በቃህ የምንልበት ጊዜው አሁን ነው እንላለን ፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጵያ እዝ

No automatic alt text available.

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *