የቀድሞ የአንድነት ለዲሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀል ሰላማዊ ትግሉን ወደፊት ያስኬደዋል!!

የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰኞ ጥቅምት 27/2010 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራሮች እና አባላት የወሰኑትን እጅግ ብስለት የተሞላበት ውሳኔ በማድነቅ ውሳኔያቸው ለሕባችን የተሻለ አማራጭ ይዞ መቅረብን የሚያስችል መሆኑን በመተማመኑ በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀፅ 5 ንዑስ አንቀፅ 2/3 መሰረት የእጩ አባልነት ጊዜያቸውን ሳይጠብቁ በሙሉ አባልነት ፓርቲውን እንዲቀላቀሉ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ቀደምም በ2007 ዓ.ም የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በሙሉ አባልነት ተቀብሎ የነበረ ሲሆን እኒሁ አባላት እና አመራሮች በፓርቲው መዋቅር ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሰላማዊ ትግሉን እየመሩ ይገኛሉ፡፡
የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቀጣይ አብረው ለመታገል የወሰኑትን አመራሮች እና አባላት ለመቀበል የእንኳን ደህና መጣቹ ፕሮግራም እንዲያዘጋጅ እና ፓርቲው ባለው መዋቅር ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋፅሆ እንዲያደርጉና የተጀመረውን የአንድነት የትግል ጉዞ እዲያስተባብሩ ሦስት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎችን በመሰየም ስብሰባውን አጠናቋል:

ሙሉ መግለጫውን እዚህ ያንብቡ…

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *