“የኦሮሞ ደም የኔ ደም ነው!“ ማለት የሱማሌውም፥ የትግሬውም፥ የጋምቤላውም፥ የሱርማውም ወዘተ የኔ ነው ማለት አይደለምን?

ለዚህ ፅሁፍ መነሻ የሆነኝ በዩቲዩብ ላይ ተለቆ ያየሁት “ነቀምት የሞቱት ትግሬዎች ዛሬ ባይሞቱ ነገ ይሞቱ ነበር” የሚል የቪዲዮ ክሊፕ ስላቆሠለኝና
ስላሰቀቀኝ ነው። ምን ዓይነት በሽታ፥ ማን እንደዚህ አድርጎ እንደለቀቀብን እጅግ የሚገርም ነው። ምን ዓይነት ዐዕምሮ ነው እንደዚህ የሚያስብ? ምን
ዓይነት አንደበት ነው ይህን ደፍሮ የሚናገር? ምንስ ድፍረት ነው በብዙሀን መገናኛ ይህን ንግግርና ምስል የሚያሰራጭ? በቅድሚያ ለሞቱት
ኢትዮጵያውያን የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን ለወዳጅ ዘመድ እየገለጽኩ እግዜር መጽናናቱን እንዲሠጣችሁ እለምናለሁ። ተዉ እየተባሉ፥ በክፋት
ፖለቲካውን በዘር ቃኝተው፥ ለዕርስ በዕርስ ዕልቂት አዘጋጅተውን፥ ኮሽ ባለቁጥር እየሮጥን አንዳችን በሌላችን ላይ እጃችንን እንድናነሳ የሚያነሳሱንን
ደንቆሮ መሪዎች ለፍርድ የሚቀርቡበት ቀን ሩቅ እንደማይሆን ተሥፋ አደርጋለሁ።
ይህን ክሊፕ ያየሁት ዕሁድ 11/05/2017 (እንደ አሜሪካውያኑ አፃፃፍ) በዩቲዩብ ነበር። ማስፈንጠሪያውን ለማያያዝ በማግስቱ መረቡን
በቻልኩት መጠን ባስስ አጣሁት። ሙዋቾች ትግሬ አለመሆናቸው ተረጋግጦ ይሁን፥ ባለመልእክቱ ተገቢ አለመሆኑን ተረድቶ ይሁን፥ ወይም ምክር
ሰምቶ ብቻ ክሊፑ ድራሹም የለ። ዘግይቶም ቢሆን ስህተትን መረዳት በጎ ተግባር ነው። ግን ደጋፊዋችና አድናቂዎች፥ እነዚህ ነገሮች የማንን ማንነት
ይጠቁማሉና ትምህርት ወስደንበት ልናልፍ ይገባል ብዬ ክሊፑን ስለለጠፈው ሰው ሌሎች ሠነዶችን ፈልጌ ተመለከትኩ። ባለጉዳዩ በቅርብ ጊዜ ውስጥ
በግጥም ችሎታውና በአማራ መደራጀት ዙሪያ ጥብቅና በመቆም፥ ወዳጆቹ እያጎሉት የመጡ ስለሆነ በሥሙም ጉግል ብታደርጉ ብዙ ማስረጃዎችን
ማግኘት ስለሚቻል እኔም ያደረግሁት ይህንኑ ነበር። አንድ በሥልክ የተደረገ ኮንፈረንስ የድምፅ ሠነድ አገኘሁና ጊዜዬን አጠፋሁበት። በዚህ የድምፅ
ሠነድ ውስጥ ጠያቂዎች በጣም ብዙ ሰዎች፥ ተጠያቂና መልስ ሰጪ ይኸው ባለጉዳያችን ነው፤ ተነስቶ ያልተጣለ ሀሳብ የለም። በጣም ብዙዎቹ
አድናቆታቸውን ገለፁ። እንደውም አንዱ ከዛች ቀን ጀምሮ የግል ጠባቂ እንደሚሆነው ይናገራል። ጥቂቶች ፀረ ወያኔ ትግሉን እንዳይጎዳ ከሌሎች ጋር
እንዳይጋጭ መከሩት። ግን አልሰማቸውም። ይህን ስሰማ ለአድናቂዎች ማሳሰቢያ መሥጠት ከጀለኝ። ይህ ሰው ጣራ በሌለው ሜዳ ላይ፥ የነተበ ሠሌን
ላይ ተኝተው ኢትዮጵያን ከወረደችበት መቀመቅ ለመታደግ መከራቸውን የሚያዩትን ውድ ታጋዮች፥ ሥማቸውን አውርዶ እየፈጠፈጠ ጭቃ ይቀባል፥
አድናቂዎች እሱን ከፍ ታደርጉታላችሁ። ደጋፊዎችና አድናቂዎች የሠሩት ሥህተት መቀመቅ ያወረደን የቅርብ ጊዜ ትዝታ አለንና እስቲ ሁለቱን
እንጎንጭ። ጭብጨባ ያሰክራል
፩. የቱን
አብዮት ያካሄዱት የበታች ሹማምንት፥ “ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዝብ በኛ ሊመራ እሺ አይልምን” አስበው፥ ብቁ ብለው ያመኑበትን
ጄኔራል እየፈለጉ ከፊት እያስቀመጡ እነሱ ከሁዋላ ሆነው ያሾሩት ነበር። አማን አንዶም አልታዘዝ ብለው ገለል እንዳሉም ወይም ገለል እንደተደረጉም፥
እነሻለቃ በራስ መተማመን ያንሳቸው ስለነበር፥ እንደለመዱት ከሁዋላ የሚሠሩትን እየሠሩ ከፊት ጄኔራል ተፈሪ በንቲን አቁመው ነበር። ተማሪዎች
በሠልፍ እያለፉ በነበረበት ወቅት፥ ጄኔራሉን ዘለው፥ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበሩን ንቀው ምን እንደነካቸው እንጃ፥ ለልጅ ይገለጥለታል ይሉ ነበር
እንኩዋን፤ “መንግሥቱ ቆራጡ ቪቫ” እያሉ ያን ቀን ሻለቃውን ወደ ዙፋን፥ እነሱን ወደ ቀብራቸው የሚወስዳቸውን መንገድ ጠረጉ።
፪. ኢዴፓን የመሠረቱ ዕውቀት ያልጠገቡ ኮበሌዎች፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ በትምህርት ያምናል፥ (በወረቀት ያምናል ሊሆን ይችላል ቃሉን
አላስታውሰውም) ብለው ያውም ከአንድም ሁለት ምሁራንን አድነው፥ የድርጅታቸው መሪ እንዲሆኑ አድርገው ነበር። እነሡ አንችለውም ብለው፥
ቢያንስ ለተወሰነም ጊዜ የተቆጠቡበትን ሥልጣነ ሕዝብ፥ አፍሠን አጎናፀፍናቸው። ሁዋላ የሥልክ ቀፎ ሁሉ በምሣሌያቸው ልንሠይም፥ ማንዴላ እያልን
ተሸክመን ጨፈርን። ያን ቀን የሰው ጫንቃ እንደሚመች አሳየን። ያን ቀን ማንዴላን ኢትዮጵያ ውስጥ ገድለን ቀበርነው። ያን ቀን ቅንጅት ላይ ከውስጥ
ሊተኮስ የሚችለውን ጠመንጃ አጉርሠንና አቀባብለን አቀበልን።
ይኸው ከስህተታችን ሳንማር፥ ቃሉን አልደግመውም፥ ከላይ የተባለውን ከተናገረ ጎረምሣ ጋር ተኮልኩለን “ግፋ” እያልን ነው። በአንዲት አገር ውስጥ
ይኸ ሁሉ የፖለቲካ ድርጅት መፈልፈሉ አንዱ ምክንያት የሥልጣን ፍላጎት መሆኑ መቸም አይካድም። ሥልጣን ደግሞ ለሌሎች ሕይወት እንደማይራራ
ከራሣችን ታሪኮች ዕልፍ ምሣሌዎችን እየመዘዝን ልናወጋ ይቻለናል። ይህን ማሥቆም የምንችል እኛው ነን። ድጋፋችንን በልኩ እናድርግ። እንደዚህ
ዓይነት ምልክቶች የደግ አይደሉምና እንደ የዕድገት በህብረት ዘማቾች መታረጃችንን አናቀብል። ጭብጨባ ያሰክራል። ላንዳንዱማ አብሾ ይሆንበታል።
10.11.2017 “የኦሮሞ ደም የኔ ደም ነው!“ ማለት የሱማሌውም፥ የትግሬውም፥ የጋምቤላውም፥ የሱርማውም ወዘተ የኔ ነው ማለት አይደለምን? (ድንበሩ ደግነቱ)
አብሾ ካልሆነ ምንድን ነው “ነገ ይሞቱ ነበር።” ብሎ የሚያናግር ነገር። ግጥም መፃፍ፥ ቅኔ መዝረፍና ኢትዮጵያን የሚያክል ውስብስብ የፖሎቲካ
ችግሮች ያሉባትን ሐገር መታደግ ለየቅል ናቸው። ሰው በዘር ማሰብ ሲጀምር የራሡን ዘር አፍቅሮ ሌሎቹን፥ የችግሬ ምንጭ ነው ካለው ዘር ጋር በዘር
የሚገናኙትን በሙሉ ላይ ጥላቻን ይፈጥራል። ሰው በጥላቻና በሥልጣን ፍላጎት ልቡ ከነደደ ለሌሎች ጆሮ የሚከብዱ የጭካኔ ተግባሮችን፥ እሡ ግን
እየጣፈጠው ነው የሚያከናውናቸው። ይኸው የሰማነውን ነገር ያናግራል። ዕድሉን ሲያገኝ በተግባር ለማድረግ ወደሁዋላ አይልም።
በዘር ዛር መለከፍ (የወዲ ዜናዊ መንገድ)
መለስ ዜናዊ ከታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅ፥ ፕሮፈሠር መሥፍን ጋር ባደረገው የመጀመሪያም የመጨረሻ ውይይት፥ ፕሮፈሠር “የአማራ ብሔርተኝነት የለም
ምርምር አድርጌ ነው እዚህ የደረስኩት ግን አንተ ልትፈጥረው ትችል ይሆናል።” ብለውት ነበር። መለስ አላዋቂነቱን ለመደበቅ በዕለቱ ቢዘላብድም
የፕሮፌሠርን ምክር ለምን ክፉ ዓላማ ሊጠቀምበት እንደሚችል እያሰላሰለ ነው ከዛ መድረክ የተሰናበተው። ከውይይታቸው በሁዋላ፥ ብዙም አልቆየ
“የአማራ ብሔርተኝነት ይጠንክር!” የሚል መፈክር በየአደባባዩ እንዲሠቀል ተደረገ። ታምራት ላይኔ ወደባሕርዳር ተልኮ፥ ከክልሉ ውጪ ያለው አማራ
“ሊጨፈጭፍ ነውና ወደዛ የሄደው፥ ቢጨፈጭፉት እኛ አያገባንም” ብሎ አፉን ሳያደናቅፈው ተናገረ። ወደ የአገሪቱ ምሥራቅ ክፍልም ተልኮ “ያኔ
ሽርጣም ሲሉዋችሁ የነበሩትን እሁን አሳዩዋቸው።” ብሎ ሰበከ። መለሥ እራሡ መቀሌ ሄዶ ከሌላው የተለያችሁ ወርቅ ሕዝቦች ብሎ ቀሰቀሰ። ለብልህ
ከዚህ በላይ አይመክሩም፥ ጨርቅ ጨርቁን እራሡ መንጥሮ ያጠራል – ቢያንስ ይህ ነበር ስሌቱ። በኢትዮጵያ ቴለቪዥን እና ሬዲዮ፥ የኦሮምኛ
ፕሮግራም ላይ እነ ሣሙዔል ዳባ ነፍጠኛ (ዐማራ ነው የሚል ስምምነት ነበር) በተገኘበት ሁሉ እንዴት ሊገደል እንደሚገባ ሥልጠና ሰጡ። ይህ ሁሉ
የተደረገው በዐማርኛ ተናጋሪው ላይ በግል የተለየ ጥላቻ ነበር ከሚለው ምክንያት በላይ፥ ኢትዮጵያዊነትን ለማዳከምና ኢትዮጵያን ተሙዋጋች
ለማሳጣት ነበር የሚለው ውሀ ይቁዋጥራል።
አንድን ብሔርተኝነት ለማጠናከር ተጠቅቶ እንደነበር በጥልቅ እንዲሰማው ማድረግ፥ የተለየ ዘር እንደሆነ መስበክ፥ የተለየ ጥቅም እና ክብር
እንዲጎናፀፍና ያንንም እንዳያስነጥቅ ማስጠንቀቅ አንዱ ዘዴ ሲሆን፥ ሌላው ደግሞ እያሳደዱ መጨፍጨፍና ግፍ መዋል ነው። በአማርኛ ተናጋሪው ላይ
የተደረገው ይህ ሁለተኛው ዘዴ ነው። ፕሮፌሰር አሥራት የአማራ መጨፍጨፍ ዛሬ ከቆመ ነገ መዐሕድን አፈርሠዋለሁ ይሉ ነበረ። ዛሬም ለዐማራ
ድርጅት መፈጠር የሚባዝኑት የዐማርኛ ተናጋሪው ተለይቶ መጨፍጨፍ ነው ምክንያታቸው። ግን ባሁኑ ጊዜ ያልተጨፈጨፈ ወይም በመጨፍጨፍ
ላይ የሌለ ኢትዮጵያዊ የኅብረተሰብ ክፍል አለመኖሩ ነው ቅራኔው።
መለስ እየዞረ ሲያጭበረብር ጥሩ ኦሮሞ ሆኖ ጥሩ ኢትዮጵያዊ መሆን፥ ጥሩ አፋር ሆኖ ጥሩ ኢትዮጵያዊ መሆን ይቻላል ይል ነበር። እውነቱ ግን ኃይሉ
ዮሐንስ እንዳለው ውጥሩ እንዲላላ የላላውን ወጥር ነው። አንዱን ስታጠብቀው ሌላው ይላል። ይህ ባይሆን የመለስ ዘመቻ ለሩብ ምዕት ዐመት
ተካሂዶ፥ ቁጥራቸው ለመቶ ሺ የሚጠጋ ዜጎች የኛ አይደላችሁም ተብለው ተፈናቅለውና፥ ተዘርፈው በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ታጅበው፥ ማረፊያ
አገር ፍለጋ ባልባዘኑ ነበር። ለኢትዮጵያ ለመሙዋገት ዜጎችዋን ሁሉ ዕኩል ማፍቀርና ማክበር፥ ለሰብአዊ ነፃነታቸው መቆም እንጂ፥ አንድን ዘውግ
ማጥበቅ አይደለም። መለስ ከመቃብር ሆኖ የሚመራው ህወሃትን ብቻ ሳይሆን እነዚህ የዘውግ መብት አቀንቃኞችንም መሆኑ የሚገርም ነው። ዩጋንዳ
ውስጥ ለደቡብ ሱዳን ተፈናቃዮች መሬት ሰጡ የሚል ዜና በአልጀዚራ ሰምቼ ከጅጅጋ ተፈናቅለው የሚንከራተቱ ወገኖቼን ሳስብ አመመኝ። አጥብቄም
አለቀስኩ። አጥብቀን ማስገንዘብ የምንፈልገው ነገር መደራጀት መብት መሆኑን ብንቀበልም፤ የአማራን ድርጅት ፈጥረን ለኢትዮጵያ አንድነት እንታገላለን
የሚለውን ገለፃ፥ ከራሣችን ቁስል የተማርን በመሆኑ አናምንምና አታላግጡብን። ይሄ ከመለስ ዶክትሪን ይቃረናል። የአማራ ብሄርን የፈጠረውና
ብሔርተኝነቱንም ያጠናከረው፥ ለኤርትራውያን አገር ሠጥቶ ኢትዮጵያን እንደነሣቸው ሁሉ፥ ለአማራም ክልል ሠጥቶት ከኢትዮጵያን ሊነቅለው ፈልጎ
ነው።
“ነገ ይሞቱ ነበር”!!!!!!
በቀንድ ከብት ገበያ አካባቢ የሚውሉ አንዳንድ ሥራ ፈላጊዎች፥ ሸማቾች ከብት ገዝተው ወደ መኖሪያቸው ገራሙን ከብት እየነዱ ሳሉ በመጠነኛ ዋጋ
በሬውን እመኖሪያቸው ድረስ ለማድረስ እንዲፈቀድላቸው ይጠይቃሉ። ምናልባትም የበሬውን ገራምነት አይተው በራሥ መተማመን ያድርቦትና
10.11.2017 “የኦሮሞ ደም የኔ ደም ነው!“ ማለት የሱማሌውም፥ የትግሬውም፥ የጋምቤላውም፥ የሱርማውም ወዘተ የኔ ነው ማለት አይደለምን?
በዛውም ወጪ ለመቀነሥ ብለው ጥያቄያቸውን ሳይቀበሉ ይቀራሉ። ጥያቄያቸው ፈቃድ ያላገኘው ሠንጋ ነጂዎች ውንብድናቸውን አሁን ይጀምራሉ።
ለዚሁ ብለው የታጠቁትን መሣሪያ እርሦ ሳያስተውሉ ያወጣሉ። አይሸበሩ መሣሪያው ሽጉጥ አይደለም። ትንሽ መርፌ ነች። እርሦ ሳያስተውሉ በሬውን
ከሁዋላው በመርፌዋ ጠቅ ያረጉታል። በሬው ይበረግጋል – ይፈረጥጣል። በነሱ ቁዋንቁዋ ፊጋ ይሆናል። በሬውን ለመያዝና እቤትዎ ለማድረሥ
ድርድሩ በእነሱ አሸናፊነት ይጠናቀቃል።
እነዚህ በውል ሳይጤኑ የሚተላለፉ ዜናዎችና መልዕክቶች ወይም ሆን ተብሎ የሚሸረቡ ደባዎች፥ ጣጣቸው እንዲህ በቀላሉ የሚቀለበስ ስለማይሆን
ከሥር ከሥሩ እየተከታተልን ልናርማቸው ይገባል። ባሁን ጊዜ በአገር ውስጥ እየተደርጉ ያሉ ዓመፆች ከመቸውም በበለጠ አስተውሎት የተሞላባቸውና
ከቀን ወደ ቀን በተቻለ መጠን ሠላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ላለማድረሥ ጥንቃቄ የሚያደርጉ ናቸው። ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ጨርሶም የለ። በፍፁም
ተገቢ ነው ተብሎ ባይታመንም ጥቃት የሚደርሥበት ሰው የህወሀት አባልና የሕዝቡ የነፃነት ጉዞ እንቅፋት ሆኖ ወይም በመሆን ተጠርጥሮ ነው።
ታዲያ አንድ “በህወሀት አባልነት የተጠረጠረ ተገደለ” ከማለት ይልቅ “አንድ ትግሬ” ተገደለ ብሎ መዘገብ ክፋት፥ ጥላቻ፥ ወይም መበታተኑን
ለማፋጠን የሚደረግ ዘመቻ ከመሆን የዘለለ ምክንያት ይኖረዋል ብሎ መገመት የማይታሰብ ነው። በሬ ነጂዎቹ በሬውን እንደሚወጉት፥ ሆን ተብሎ
ተመሳሳይ ቁዋንቁዋዎችን እየተጠቀሙ፥ ትግርኛ ተናጋሪውን በማስበርገግ ከኢትዮጵያዊነት ጥላ ለማውጣት፥ ተመሳሳይ እርምጃ በሌሎችም ላይ ከውኖ
ሁሉም በየፊናው ሲበረግግ የአማራ አገር በቀላሉ ለማግኘት የሚሸረብ ሤራ ይመስለኛል። አማርነት ወንጀል እንዳልሆነው ሁሉ ምንም ነገር፥ ህወሀት
እስከዛሬ የገደለውን ሁሉ ደምሮ በመቶ አባዝቶ እንኩዋን በተጨማሪ ቢጨፈጭፍ፥ በኢትዮጵያ ምድር ትግሬነትን ወንጀል ሊያደርግ የሚችል በቂ
ምክንያት ሊገኝ አይችልም። ወንጀል የግል ነው። እያንዳንዱ በጥፋቱ ልክ ፍርዱን ይቀበላል። በዘር የሚሄድ ነገር የለም።
ዛሬን የምንኖርበት ምንም በቂ ምክንያት የለንም። የነገ ተሥፋን ስናስብ ግን ልባችን ይሞቃል። ነገ ሥልጣን የሕዝብ ነው የሚሆነው። ነገ የትግራይ
ተወላጅ በኢትዮጵያዊነቱ ልቡን ነፍቶ ነቀምት ውስጥ እስከ ንፅሕናው የሚንጎባለልበት ቀን ነው። አንድ የኦሮሚያ ተወላጅ መቀሌ ላይ ቤት ገዝቶ እስከ
ሙሉ ክብሩና ኩራቱ የሚኖርበት ቀን ነው። ነገ የፍትሕ ቀን ነው። የዕኩልነት ቀን ነው። በዘር ተለይቶ የሚደረግ አድልዎ አይኖርም። ነገ እሥር ቤቶች
ሁሉ ባዶ ሆነው ወደ ትምህርት ቤትነት የሚቀየሩበት ቀን ነው። ምግብ መለመን የምናቆምበት ቀን ነው ነገ። ይኸው ዛሬ ኢትዮጵያውያን የጀመሩት
ደማችን አንድ ነው ዘመቻ እየጋለና እየበሰለ ሄዶ ሁሉም ማንም ሊለያቸው በማይችል ሁኔታ የራሣቸውን እድል ዕራሣቸው ሊወሥኑ እንጂ ግዩር
(ዲያስፖራ) ላያለያያቸው ተቃቅፈዋል። የኦሮሞው ደም የኔ ደም ነው የተባለውኮ በወቅቱ ፉካዎችን ሁሉ የሞላው ኦሮሚያ ተብሎ በተካለለው
የአገራችን ክፍል የሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ በተደረገው ጭፍጨፋ የፈሠሠው ደም በመሆኑ ጭፍጨፋው በአስቸኩዋይ እንዲቆም ለመጠየቅ እንጂ
የሌላው ኢትዮጵያዊ ደም የተለየ ነው ለማለት አልነበረም። እንጂ የሱማሌውም፥ የትግሬውም፥ የጋምቤላውም፥ የሱርማውም የአደሬው፥ የጉራጌው፥
የከምባታው፥ የአፋሩ፥ የዶርዜው፥ አረ ሥንቱ ተጠቅሶ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ደም ከቁዋንቁዋው ልዩነት በላይ የተዋሀደ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ
ሆነናል መጥኔ ለከፋፋዮች። የሞቱት አንዴ ሞተዋልና ልናሥነሳቸው ባንችልም ነገ ሞት እንደሌለ ግን ተሥፋ እናደርጋለን። ብቻ አንድ ላይ እንቁም።
**ማሳሰቢያ ለጋዜጠኞች
ብዙ ጊዜና በተደጋጋሚ ህወሀትን ለመጥቀስ “የትግሬ ነፃ አውጪ” ወይም ተመሳሳይ ስም ስትጠቀሙ ይሰማል። አንድን ሰው መጥራት ያለብን በእራሡ
ወይም በወላጆቹ በወጣ ስም ነው። ሥሙ “ህወሀት” ነው። በአንድ ቃል “ወያኔ” ነው። ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ጠፍሮ የያዘው፥ የገደለው፥
ያስጨፈጨፈው ነው እንጂ ነፃ አውጪው አይደለም። ቢሆንስ ከማነው ነፃ የሚያወጣው። አፍኖ የያዘው እራሡ ህወሃት ነውኮ። ስለዚህ እባካችሁ
በየዘገባዎቻችሁ ከወያኔ ወይም ከህወሀት ውጪ ከትግራይ ሕዝብ ጋር አያይዛችሁ ወያኔን አትሰይሙ – እንድምታው ደግ አይደለምና።

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *