ኮከብ አልባውን ሰንደቅ አላማ በአዲስ አበባ ስታዲየም የፓውዛ ማማ ላይ የሰቀለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ኮከብ አልባውን ሰንደቅ አላማ በአዲስ አበባ ስታዲየም የፓውዛ ማማ ላይ የሰቀለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ በአዲስ አበባ ስታዲየም የፓውዛ መብራት ማማ ላይ ኮከብ አልባ የሆነው አርንጋዴ ቢጫ ቀዩን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የሰቀለ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰማ። ግለሰቡ በእለተ ሰንበት ማለዳ ሰንደቅ አላማውን መስቀሉ ብቻ ሳይሆን ከማማው ላይ ይህን ሰንደቅ አላማ ለብሶ አልወርድም በማለት በቦታው የተገኙትን የፓሊስ ሃይሎችን ሲያስጨንቅ ታይቷል።

የኮከብ አርማ ከሌለው ሰንደቅ አላማ ስር በግልጽ ለማየት የሚያስቸግር ምልክት ያለበት ሌላ ባንዲራንም በዚሁ የፓውዛ
ማማ ላይ ግለሰቡ ሰቅሏል። ግለሰቡ ከብዙ ልመናና ማግባባት በሃላ በፖሊስና በእሳት አደጋ ዘመናዊ መኪና ከማማ ላይ ባንዲራውን እንደለበሰ
ለመውረድ መቻሉንም ታውቋል። በቦታው የደረሱት የእሳት አደጋ እና የፖሊስ ሃይሎች በዘመናዊ መኪና ግለሰቡ የሰቀለውን ሰንደቅ አላማ ለማውረድ
ጥረት ሲያደርጉ ታይተዋል። የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እንዲህ ያለ ድፍረት በሚጠይቅ ስነ ልቦና በፓውዛው ላይ የሰቀለው ግለሰብም በፖሊስ
መኪና ተጭኖ መሄዱን ለማወቅ ተችሏል። ከፍተኛ ቁጥጥር በሚደረግበት በመዲናችን አዲስ አበባ እንዲህ አይነት ድፍረት የሚጠይቅን ድርጊት ለመፈጸም አይደለም
ለማሰብ ከባድ በሆነበት በዚህ ወቅት ሰንደቅ አላማውን በስታዲየሙ የፓውዛ ማማ ላይ መስቀሉ በብዙዎች አነጋጋሪም
አስደናቂም ሆኗል።

 

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *