በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች መከላከያው ይውጣ በሚል ዓመጽ መጀመራቸው ተሰማ 

በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ ያለው የመከላከያ ሰራዊት ከመካከላችን ካልወጣ በማለት ነዋሪው የስራና ትምህርት
ማቆም አድማ እያካሄደ መሆኑ ታወቀ።
በምስራቅ ኦሮሚያ የሃሮማያ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች መከላከያ ሰራዊት ግቢውን ለቆ ካልወጣ ትምህርት አንማርም በማለት
አድማ ከጀመሩ ዓስር ቀን እንደሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ተማሪዎቹ በሰራዊት ተከበን የምንማርበት ምክንያት የለም
በማለት ትምህርታቸውን እንዳቆሙ ተገልጿል።
የመከላከያ ሰራዊት መስፈር ያለበት በከተማም ሆነ በገጠር ሳይሆን በተወሰነለት ወታዳራዊ ካምፕ ውስጥ ብቻ እንደሆነ
ሕጉ ቢያዝም ስርዓቱ ግን የሀገር ድንበር ጠባቂ የሆነውን መከላከያ ሰራዊት ለድርጅታዊ ጥቅም ሲል በህዝብ ውስጥ በማስፈርና በማሰማራት በንጹሃን ላይ እርምጃ እያያስወሰደ እንዳለ ይነገራል።
ይህንን የመከላከያውን እርምጃ በማውገዝ እየተቃወሙ ካሉት ውስጥ በምስራቅ ወለጋ ያሉ ከተሞችም የሚጠቀሱ ሲሆን የአካባቢው ህዝብ መከላከያ ሰራዊቱ ካልወጣ አንዳችም ተግባርና አገልግሎት አንሰጥም ብሎም በስራም ላይ አንሳተፍም  በማለት የንግድና ስራ ማቆም አድማ እያካሄደ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
በኦሮሚያ፣ በአማራና ሌሎች ስፍራዎች ውስጥ በሚካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ ተሳታፊ የሆኑትን ንጹሃንን በግፍ በመግደል ገናና ስምና ዝናን እያተረፈ ያለው መከላከያ ሰራዊት በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞና ጥላቻን እንደፈጠረ
ለማወቅ ተችሏል። በምስራቅ ወለጋ ከተሞች የሚኖሩ ነጋዴዎች፣ ሰራተኞችና ተማሪዎች በጋራ ሆነው የመከላከያ ሰራዊቱ ከመካከላችን
ካልወጣ የምናካሄደው አንዳችም የንግድ ልውውጥም ሆነ የምንሰጠው አገልግሎት የለም በማለት የንግድ ተቋሞቻቸውን
በመዝጋት በስራ ማቆም አድማ ላይ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። በተያያዘ ዜናም በሀረሪ ክልል የታወጀውን የአስቸካይ ግዜ አዋጅና የተቋቋመውን ኮማንድ ፖስት በዞኑ ያለው የኦህዴድ ጽ/ቤት እንደማይቀበለው አስታውቋል።
የሀረሪ ክልል በአደጋ ላይ ነው በማለት በሳምንቱ አጋማሽ ላይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ቢታወጅም ኦህዴድ ግን አዋጁ
አይመለከተኝም በማለት እንደማይቀበለውና እንደማይተገብረው ገልጿል።

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *