መንግስት ምንም አይነት ሰልፍ እንዳይካሔድ እገዳጥያለሁ ሲል አስታወቀ

በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በዚህ በአሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ ምንም አይነት የሰላማዊ ሰልፍ በኢትዮጵያ ዉስጥ
መካሔድ የለበትም ሲል እገዳ መጣሉን የአገሪቷ የዜና አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።
የሰልፉ መታገድ በዋናነት ያስፈለገዉ የአገሪቷን ሰላም እና መረጋጋት ለማጠናከር የሚል ምክንያት በአገሪቷ ባለስልጣናት
እየተነገረ ይገኛል።
የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እየደረሰ ያለውን የሰው እና
የንብረት ጥፋትን ለመከላከል የእገዳ ውሳኔ ላይ የደረስነው ምክር ቤቱ ተወያይቶ ሙሉ ስምምነት ላይ በመድረሱ ነው
በማለት ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ዉስጥ በተለይ የ10 ወር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነሳ በኋላ የሕዝባዊ አመጹ በተለያዩ የአገሪቱ
ክፍሎች በከፍተኛ ደረጃ እየተቀጣጠለ ያለ መሆኑን ያመኑ ሲሆን ይህን እንቅስቃሴም በተለያዩ ባለስልጣናት የተደገፈ እና
የተበረታታ እንደመሆኑ ይህንን ድርጊት በተባበሩ እና ችግሩን ለማስወገድ ኃላፊነታቸዉን ባልተወጡት ላይ ክስ
እንደሚመሰርቱም ጨምረው ገልጸዋል።
የደህንነት መስሪያ ቤቱን ስብሰባ በሊቀመንበርነት የመሩት የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦታ አቶ ኃይለማርያም ፤ ሲሆኑ
ከአገራችን ድህነትን ለማስወገድ ዋናው እና ቁልፍ ነገር ሰላም እና መረጋጋት ነው በማለት የጉዳዩን አሳሳቢነት
መግለጻቸዉን የአገር ዉስጥ የዜና አዉታሮች ዘግበዋል።
በስብሰባውም ላይ የክልሎች አስተዳዳሪዎች፤ የየክልሉ የደህንነት ኃይሎች እና የየከተማዎቹ ከንቲባዎች መገኘታቸውም
ታዉቋል።
ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት በኋላ በአገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎች በርካታ የሆኑ ግጭቶች እና የሕዝብ አመጾች
መነሳታቸውን ተከትሎ አገዛዙ ለመቆጣጠር ያልቻለበት ሁኔታ እንደተፈጠረና ይህ ሕዝባዊ አመጽም ፖለቲካ ጥያቄን
በማንገብ አገዛዙ ስልጣንን ለሕዝብ እንዲያስረክብ መጠየቅ ደረጃ ደርሷል። ይህም ጥያቄ በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ስጋት
እንደፈጠረበት ለማወቅ ተችሏል።
መንግስት በአገር ዉስጥ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመጽ ስጋት ዉስጥ መግባቱን ተከትሎ ለ3 ተደጋጋሚ ጊዜ በመቀሌ
ቢሰበሰብም ምንም አይነት የመፍትሔ ሃሳብ ላይ ሊደርስ ባለመቻሉና ይባስ ብሎም በሕውሐት ዉስጥ ያለመግባባት
ተፈጥሮ ድርጅቱን ለሁለት መክፈሉ ተጨማሪ ራስ ምታት እንደሆነበት የሚወጡት መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ከዚህ በተጨማሪም በውጭ አገር ያለው ኢትዮጵያዊ በአሜሪካ መንግስት የHR 128 ረቂቅ ሕግ እንዲጸድቅ
የሚያደርጉት ጥረት አገዛዙን ወደ ከፋ ችግር ላይ እንደጣለው የሚታወቅ ነው።

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *