ጦር አዛዡ ከነወታደሮቹ ለአሰሳ እንደ ወጣ መቅረቱ ተሰማ

በሞያሌ አካባቢ ሰፍሮ ከሚገኘው 10ኛ ክ/ጦር ውስጥ በአንድ ሀይል አዛዥ የሚመራ ቡድን ለአሰሳ እንደወጣ መቅረቱን
ተከትሎ የተሰወሩትን ወታደሮች ፍለጋ የወጡት የክ/ጦሩ በርካታ ወታደሮች ኬንያ ድንበር መድረሳቸው ታወቀ፡፡
ባለፈው ሰኞ ህዳር 11 ለአሰሳ በሚል የወጣውና በአንድ የሀይል አዛዥ የሚመራው ቡድን ከነሙሉ ትጥቁ የተሰወረ
መሆኑ የታወቀው ከዋናው ማዘዣ ጣቢያው ጋር የነበረው ግንኙነት ከተቋረጠ በኋላ ሲሆን በማግስቱ ማክሰኞ ህዳር 12
ፍለጋው ቦረናና ዋቤሎን አካባቢ አድርሶ ኬንያ ድንበር መድረሱም ለማወቅ ትችሏል፡፡
የ10ኛ ክ/ጦር አካል የሆነውና በአንድ የሀይል አዛዥ የሚመራው ቡድን በስሩ ይዞዋቸው የነበሩት ወታደሮች ቁጥር ግን
እስከ አሁን አልተገለጸም።
ከተሰወሩት ወታደሮች ውስጥ የተወሰኑት በቅርቡ የማእረግ እድገት ያገኙ እንደሚገኙበት ኢሳት በዘገባው አስፍሯል።
በርካታ ወታደሮች በተሳተፉበትና እስከ ኬንያ ድንበር በደረሰው የፍለጋ አሰሳ ስለ ተሰወሩት ወታደሮች ሁኔታ የተገኘ
ፍንጭ ያለመኖሮን በተጨማሪ ተዘግቧል።
የወታደሮቹ መሰወር በቅርቡ በቦረና አካባቢ ተከስቶ ከነበረው የሶማሌና ኦሮሞ ግጭትን ተከትሎ በክ/ጦሩ ውስጥ
ተሰምቶ ከነበረው ተቃውሞ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል፡

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *