የፌዴራል ፖሊስ አባል የሆኑ አንድ ኮማንደር በባህር ዳር በጥይት ተመተው ህይወታቸው አለፈ 

በባህር ዳር ከተማ በፌዴራል ፖሊስ መስሪያ ቤት ተቀጥረው ሲያገለግሉ የቆዩ ከፍተኛ ስልጣን ያላቸው ኮማንደር
ተገድለው መገኘታቸው ተነገረ።
ኮማንደሩ በባህር ዳር ከተማ ማክሰኞ ማምሻ ላይ በመኖሪያ ቤታቸው አከባቢ በጥይት ተመትተው ህይወታቸው ሊያልፍ
እንደቻለ የሚወጡ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ።
ኮማንደር ደስአለኝ ልጅአለም በመባል የሚታወቁት እኚህ የፌዴራል ፖሊስ አዛዥ በሰሜን ምእራብ ዞን ተመድበው
ሲያገለግሉ እንደነበረ ታውቋል።
ግድያውን ማን እንደፈጸመው ይህ ዜና እስከ ተጠናከረበት ሰአት አልተገለጸም። የሟች ኮማንደር ደስአለኝ ልጅአለም
ስርአተ ቀብር በተወለዱበት ጸለምት እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል።
በ2008 ዓ/ም የባህር ዳር ነዋሪዎች በአገዛዙ ላይ ቅራኒያቸውን ለመግለጽ ለሰላማዊ ሰልፍ ወደ አደባባይ
መውጣታቸውን ተከትሎ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በፈጸሙት ግድያ ላይ ሟች ኮማንደር ደስ አለኝ ተባባሪ ናቸው
እየተባለ ወቀሳ ይደርስባቸው እንደነበረም ተሰምቷል።
በባህር ዳር ከተማ መንግስትን በመቃወም በተደረገ ሰላማዊ ሰልፍና ህዝባዊ እምቢተኛነት የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግደላቸው ይታወሳል።

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *