የህወሃት ዝክረ ንግሥናና የአድዋ ወያኔ ድል (በሃያሬ ተንለሱ)

አልበርት ኤንስታይን እንዲህ ይላል “ጥቂት ሠዎች ከሚኖሩበት ማህበራዊ አካባቢ ተፅእኖ ውጪ በተለየ መልኩ
አስተያየታቸውን መግለፅ ይችላሉ። አብዛኛዎቹ ሠዎች ግን ይህን አስትያየት ማመንጨትም ሆነ መግለፅ አይችሉም።”
“Few people are capable of expressing with equanimity opinions which
differs from the prejudice of their social environments. Most people are even
incapable of forming such opinions.’’
የመቀሌውን የህወሃት ግምገማ አስመልክቶ የተለያዩ ግምቶችንና መላ ምቶችን ሰማን። ህወሃት በተለያዩ አንጃዎች
ስለመሠንጠቁና አደጋም እንዳንጃበበት አዳመጥን። ቀናትን ያስቆጠረው ግምገማ “ፖለቲካዊ ለውጦችን” ሊያመጣ
ይችላል በሚል ቀቢፀ-ተስፋ የአንጃውን ብዛትና የእያንዳንዱን አንጃ መሪ በሥም ዘከርን። እነ እከሌ የለውጥ ሃዋሪያቶች
እነ እከሌ ደግሞ አክራሪ ፀረ-ለውጥ ናቸው ስንል ፈረጅን። በሀሣብና በምኞት ታንኳ ወራጅ ወንዝ ላይ እየቀዘፍንና
ከአንዱ ድብ ወደ ሌላው እየተላተምን ከረምን። በአዜብና በአባይ ወልዱ መታገድና መውረድ ሳቢያ “የመለስ ራዕይ”
ተብዬው ገደል ገባ ብለን ፈነጠዝን። አንዱም ግምት ልክ አልነበረም። የባለ ብሩህ ህሊና መላ ምትም /Inteligent
Hypothesis/ አልሆነም።
ይልቁንም የህወሃት ግምገማ የተሠኘው ድራማ ባለ ሁለት ስለት ጩቤ ነበር።
1. ፖለቲካዊና የወንጀል ሴራ /Political & Criminal Conspiracy/ በየአቅጣጫው እየተቀጣጠለ፣
በዓይነቱ፣ በመጠኑና በስፋቱ እየገዘፈ የመጣው ህዝባዊ ተቃውሞ እያየለና መቀልበስ ወደማይችልበት ደረጃ እያደገ
በመምጣቱ፤ ይህም ነውጥ ለህወሃት የበላይነት በቻ ሳይሆን ለህልውናውም ፈተና እየሆነ መከሠቱ ነው። ይህን
ህዝባዊ ተቃውሞ ለማፈን ብሎም ለመደምሰስ የሚቻልበትን መንገድና ዘዴ የስብሰባው ዋነኛ አካል ነበር። ህዝባዊ
ተቃውሞውን የመቀልበሱ ሃሣብ ላይ ሳይሆን መቀልበሻው ዘዴ ላይ ልዩነትን ማስተዋል ይቻላል። ይህ ተፈጥሯዊ
ነው።
ተቃውሞውን በመጨፍለቁ ላይ የአተገባበር ልዩነት ቢኖርም በመሠረተ ሃሣቡ ላይ ግን ህወሃት ፍፁም አንድነት እንዳለው
መሳቱ ግን ፖለቲካዊ የዋህነትም ነው። ከዉጤቱ መረዳት እንደተቻለው፤ በግምገማ ስም ህወሃት የተጠራው ስብሰባ
ያተኮረው ባለ ሁለት ፈርጅ ስሌት ይህን ይመስላል።
ሀ). ህወሃት “የትምክህትና የጠባብ ሃይሎች” የሚላቸው ኃይሎች ህዝባዊ መሠረታቸው እየሰፋ በመምጣቱ ሳቢያ
የእነርሱን ጨኸት በመቀማት በተለይ “እህት ድርጅቶች” የሚላቸውን አኦህዴድና ብአዴንን የኢትዮጵያዊነት አርማን
በጊዜያዊነት በማሸከም ህዝቡን ከነዚህ “የትምክህትና የጠባብ ሃይሎች” ተፀዕኖ ማላቀቅ፤ ወይንም እነዚሁን የማደጎ
ልጆቹን ከደህንነት መዋቅሩ ጋር በማቀናጀት የጎሣንስ የእርስ በእርስ ግጭት/ Inter-tribal conflicts/
በማቀጣጠል፤ ህዝቡ የማዕከላዊ ወይም የፌደራል መንግስትን ጣልቃ ገብነት እንዲጠይቅ በማድረግ ህዝባዊ ድጋፍን
ማሠባሰብ የመጀመሪያው ስልት ሲሆን፤ ይህ ካልተሣካ ግን ወደ ሁለተኛው ስሌት ይሻገራል።
ለ). የህወሃት ትርክት እንደወትሮው የህዝባዊው እምቢተኝነት መንስዔ “የትምክህትና የጠባብ ኃይሎች” ሤራ እንጂ
ሕዝቡ የስርዐት ለውጥ ፈላጊነት አይደለም ብሎ እራሱንና አጃቢዎቹን ማሳመን ነው። ለዚህም ህወሃት ሊተገብር
11/30/2017 የህወሃት ዝክረ ንግሥናና የአድዋ ወያኔ ድል
የተዘጋጀው የነዚህ “የትምክህትና የጠባብ ሃይሎች” ድርጅታዊ ሰንሠለትን መበጠስ፣ በነርሱም ሰበብ በህብረሰቡ ውስጥ
ተራማጅና ከገዢው ህወሃት “አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ቅዠትና ዴሞክራሲያዊ ብሄረተኝነት” አመለካከት ውጪ ያሉን
የሃገሪቱን ዜጎች በጅምላ የሃይል እርምጃ በመውሰድ ማሰር፣ ማሳደድና መግደልንና ተቃውሞውን በሃይል መጨፍለቅ
ነው።
2. በእምብርትነት የሤራው ጠንሳሾችና ተቀፅላዎቻቸው /Hub-and-Spok Conspiracy/ የህወሃት
“ግምገማና ተሃድሶ” የማደናገሪያ ስያሜ የተሰጠው የህወሃት የሤራ መከሸኛ ስብሰባ ከላይ በቁጥር 1 ላይ የተገለፀውን
ህዝባዊ ተቃውሞን የማምከኛ መርሃግብር ያሣየው የህወሃትን መሠንጠቅ ሣይሆን፤ መርሃግብሩን ተግባራዊ በማድረግ ላይ
የተከሰቱን አናሣ ልዩነቶች ለማጋባትና ለዚህም አገልግሎት በሚወል አዲስ ድርጅታዊ አወቃቀርን መከለሱ ነበር። ለዚህም
የተደረሰበት የመግባቢያ ሠነድ/memorandum of understanding/ የህወሃትን ድርጅታዊ ጥንካሬ
ለመጠበቅና ጠላቶቹን “የትምክህትና የጠባብ ሃይሎች” ለመምታት ምስጢራዊ እርምጃዎችንና ሤራዎችን ለማቀነባበር፤
ህወሃትን የሚመሩትን ግለሰቦች ቤተሰባዊና ጎጣዊ ማድረጉን ያካትታል።
ከቤተሰብና ጎጣዊ መረቡ ውጭ የሆኑትን የአዜብም\ና የአባይ ወልዱ መታገድና መወገድ አንዱ ነው። የጦስም ዶሮ
ሆነዋል። የአሁኑ የህወሃት ቤተሰባዊና ጎጣዊ መረብ ፍፁም አድዋዊ (በአድዋ ተወላጆች የተሞላ) አድርጎታል። ለዚህም
ማስረጃው ከዘጠኙ የህወሃት ፖሊት ቢሮ አባላት መካከል ስድስቱ ማለትም ደብረፅዮን፣ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሄር፣
ጌታቸው አሰፋ(ደህንነት አለቃ)፣ አባይ ነብሶ፣ አብርሃም ተከስተና አዲሳዓለም ባሌማ ፪/፫ ድምፅ ያላችው የአድዋ
ተወላጆች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ሦስቱ ውስጥ ኬሪያ መሃመድ(ባሏ ከአድዋ)፣ ዓለም ገ/ዋህድ (ሚስቱ ከአድዋ የሆነች)ና
ጌታቸው ረዳ(ዱርዬው ወያኔ) ተቆጣጥረውታል። ህወሃት በአድዋዎች መዳፍ እጅ ሙሉ በሙሉ ወድቋል። ከእንግዲህ
የሚመሩትና የሚያሽከረክሩት አድዋዎች ሆነዋል። ህወሃት ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ፤ አድዋዎች በትግራይ ህዝብ ላይ
የበላይ ሆነዋል። ዛሬ ህወሃት የአድዋ – ህወሃት ነው። የአድዋም የበላይነት ማለት ፀረ- ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊ የሆኑ
የባንዳ ቤተሰቦቻቸውን አርማ ያነገቡ ሹምባሾች ፈላጭ ቆራጭነት ማለትም ነው።
3.የነቢያቸው “የመለስ ራዕይ” ዕጣ ፈንታ አንዳንድ ወገኖች የአዜብና የአባይ ወልዱ መወገድ “የመለስ ራዕይ” ግበዐተ-
መሬት ነው ብለው ያምናሉ። “የመለስ ራዕይ” ማለት የኢትዮጵያ ህዝብን “በብሔር ጭቆና” ትርክት በማደንዘዝ ወደ
ዘመነ መሣፍንት ጊዜ አስተሳሰብ በመመለስ ህዝቡን በማያባራ የእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ//Inter-tribal
conflicts/ በመክተት በሚፈጠረው የህዝብ በህዝብ መቃቃር፣ ቂም፣በቀልና መጠራጠር መካከል የትግራይን
የበላይነት ማስጠበቅ ነው። ግዙፍ ስህተት ነው። “የመለስ ራዕይ” ማለት የትግራይን የኢኮኖሚ፣የወታደራዊና የፖለቲካ
የበላይነት በጅምላ፤ የአድዋ የበላይነት በነጠላ በኢትዮጵያዊያን ላይ መጫንና የባንዳ አባቶቻቸውን ያልተሳካ ህልም
የመተግበር “ደደቢት ወለድ የሽፍታ ራዕይ”ነው። “የመለስ ራዕይ” የአፓርታይዳዊው የወያኔ ዘረኛ ስርዓት አርማና
መሠረት ነው። መንግስት ያለ ፖለቲካዊ አይዲዮሎጂ ስለማይኖር ይህን “ራዕይ” በተሻለና ከጊዜው እሣቤ ጋር
በሚጣጣም መልኩ መቅረፅ የሚችሉ ብቁ ግለሰቦች በህወሃት ሎሌዎች መሃል ባለመኖራቸው ይህን “ራዕይ” እንደ
እምነት መፅሃፍት ከመደጋገም ውጭ ምርጫም አይኖራቸውም።
ሞት ለህወሃት አፓርታይዳዊው የወያኔ ባንዳዎች ሥርዐት!

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *