በሊቢያ ጉዳይ ማን ነዉ ተጠያቂ(በልኡል አለሜ)

አሁን የአፍሪካዊያን ስቃይ እጅግ ዘግናኝ ወደ ተባለ ደረጃ ላይ ደርሷል……. አለም ግን ከማዉራት የዘለለ አንዳችም ነገር
እየፈየደ አይደለም… ማን ነዉ ተጠያቂዉ
በሊቢያ በስደት የሚንከራተቱ አፍሪካዊያን ችግር ሊቢያ ብቻ ላይ የሚያነጣጠር አይደለም ይልቁንም አለማቀፋዊ
ተደማጭነት ያላቸዉ ሐገሮች አለማቀፋዊ የስደተኞች መብት ላይ ያላቸዉ አቋም በራሱ ሌላ ችግር ነዉ። ለዚህ ትልቁን
ሚና የሚወስዱት በተለይ ፈረንሳይና ጣሊያን ሲሆኑ እጅግ ብዙ አፍሪካዊያን ወደ ሐገራቸዉ ለመግባት ሲሉ በሳሃራ
በረሃዋ መቃብር ሊቢያ ዉስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እነደሚሰቃዩ ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ ይህን ማወቅና ዝም ማለት በራሱ እንደ
ሐገር ከአለም አቀፍ ህግ ጋር ትልቅ ወንጀል ነዉ ከሁለቱ ሐገሮች መናሕሪያ የሆነችዉ አዉሮፓ በራሷ ለዚህ መልስ
እራሷን የምትዘጋጅበት መድረክ እንዲጠር አለም አቀፋዊ ጫና በአፍሪካዊያን መጀመር አለበት።
ፈረንሳይ ይህንን ተጠያቂነት ቀድማ የተረዳችዉ ይመስላል በአሁኑ ወቅት የተመድ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት
ተሟጋቾችን ጉዳይ በሊቢያ ላይ ለመነጋገር የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ም / ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እየጠየቀች
ነው። የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዣን-ኢፍስ ሌድሪን ፈረንሳይ የፍትህ ስርዓቱ በአግባቡና በፍጥነት በሊቢያ
በኩል ካልተካሄደ በሊቢያ ላይ ማእቀብ እንዲደረግ ጥሪ አቅርባለች።
የፈረንሳዩ ሚኒስቴር አንድ ነገር ማብራራት አልቻሉም። ለየትኛዉ የሊቢያ መንገስት ነዉ ማስጠንቀቂያ ወይም ማእቀብ
እንዲደረግበት ጥሪ ያቀረቡት? የትኛዉን እዉቅና የተሰጠዉን መንግስት ነዉ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠዉ የሚሞግቱት ?
በትሪፖሊ ያለዉን ነዉ ወይስ በምስራቅ በኩል ሃፍታርን የተቆጣጠረዉን አንጃ ?የቱን ነዉ መንግስት ብለዉ ማእቀብ
እንደሚደረግበት ያስፈራሩት? በወደቀች ሐገር (failed state? ) ላይ እንደምን ያለ ማእቀብ ነዉ ዉጤታማ
የሚሆነዉ የሚለዉ መጠይቅ ፈረንሳይን አላጋጭ አስብሏታል።
ለምሳሌ ጣልያንን ልንወስድ እንችላለን በሊቢያ ለሚንቀሳቀሱ የሰዉ አዘዋዋሪ ወይም አሻጋሪዎች እላፊ ገንዘብ በመክፈል
በመጡበት ጀልባ እንዲመለሱ ታደርጋለች። ይህ ለአሻጋሪዎች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ የሆነላቸዉ ሲሆን አሻጋሪዎቹ
አፍሪካዊያን ስደተኞችን በማመላለስ ገቢያቸዉን እንዲያዳብሩ ሲያደርጋቸዉ በሌላ አንጻር እንዲህ አይነት እጅግ አደገኛ
ስህተት የምትሰራዋ ጣሊያን በሊቢያ ለሚካሄደዉ ግፍ ሐላፊነት መዉሰድ ግዴታዋ እንዲሆን ያደርጋታል።
ባለፈው ሚያዝያ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ዓለምአቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) በሰሜን
አፍሪካ ስደተኞችን ሊገድሉ የሚችሉበትን ምክንያት እና “የባሪያ ገበያ”ን በተመለከተ ሪፖርት አውጥቷል. ሪፖርቱ
በአይ.ኦ.ኤም ተይዞ ወደ ትውልድ ሀገራቸዉ የተመለሱትን ስደተኞችን አስመልክቶ ነበር። በሪፖርቱም መሰረታዊ ይዘት
ከዚህ ሁሉ ደባ ጀርባ እነ ማን ሊኖሩ እንደሚችሉ ይሰነፍጣል።
ሐላፊነት በአንድ አካል ጫንቃ ላይ ለማስቀመጥ የተመቸችዉ ሊቢያ ዉስጥ የሚንቀሳቀስሱ የተለያዩ አማጺያንም ሆኑ
ሌሎች ድርጅቶች ከዚህ ሁሉ ግፍ ጀርባ ከተጠያቂነት እንዳያመልጡ የግፉና የሰቀቀኑ መሪዎች ናቸዉ። ለምሳሌ በሊቢያ
በተለይም ባለፉት ሶስት የእርስ በርስ ጦርነቶች ወቅት የሐገሪቷን ብሄራዊ ደህንነት መፈራረስን በመንተራስ በመቶዎች
የሚቆጠሩ የሊቢያ ዜጎች ተጠልፈዉ ተሽጠዋል። ለህገወጥ የጉልበት ብዝበዛ ለአካል ክፍል መበለት እና ልፍትወት ስጋ
እንዲሁም ለከፍተኛ ስቃይም ተዳርገዋል

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *