ለስብሰባ ባህር ዳር የተገኙት የምስራቅ በለሳ የምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተገደሉ

በባህር ዳር አገዛዙን በተለያየ መንገድ የሚያገለግሉ ግለሰቦች ባልታወቁ ሰዎች በሚወሰድባቸው እርምጃ ህይወታቸው መጥፋቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
በጎንደር የምስራቅ በለሳ የምክርቤት አፈ ጉባኤ ሆነው መንግስትን ሲያገለግሉ የነበሩ ግለሰብ በባህር ዳር ተገድለው
መገኘታቸው ተሰምቷል። አፈ ጉባኤ ፈንታ ታረቀኝ በተደጋጋሚ ለስራና ለስብሰባ ወደ ባህር ዳርና ወደ ተለያዩ ከተሞች
በመቀንሳቀስ ስራቸውን የሚያከናውኑ እንደነበረም ተነግሯል።
አገዛዙን ከካድሬነት አልፎ ከፍተኛ ስልጣን በመያዝ በአፈ ጉባኤነት እያገለገሉ የነበሩት አቶ ፈንታ ታረቀኝ ባልታወቀ
ግለሰብ አለያም ግለሰቦች ተገድለው አስክሬናቸው በጣና ውስጥ ተጥሎ ተገኝቷል።
አፈ ጉባኤ ፈንታ ታረቀኝ ስብሰባቸውን እስኪያጠናቅቁ በባህር ዳር በዘንባባ ፔንስዮን ተከራይተው እንደቆዩም
ታውቋል። አፈ ጉባኤው ከተከራዩበት የዘንባባ ፔንሲዮን በህዳር 20 ቀን 2010 ዓም በተወሰኑ ቡድኖች ሳይታፈኑና
ሳይጠለፉ እንደማይቀር ምንጮች ጠቁመዋል።
አፈ ጉባኤ ፈንታ ታረቀኝን በከተማው የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎች አፍነው በጥይት ገድለዋቸዋል ቢባልም ይህ ዜና
እስከተጠናከረበት ሰአት ለእርምጃው ሃላፊነቱን የወሰደ አካል አልተገለጸም።
በአፈ ጉባኤነት እያገለገሉ የነበሩት እኚህ ባለስልጣን በተለያዩ ጊዜያት በሚያደርጉት የጥቆማ ተግባር ብዙ ሰዎች
በመንግስት ወታደሮች እንዲገደሉና እንዲታሰሩ ያደረጉ እንደሆነም ከአከባቢያቸው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በባህር ዳር ከሳምንታት በፊት የፌዴራል ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ኮማንደር ደስአለኝ ልጅአለም በመኖሪያ ቤታቸው ደጃፍ
በጥይት ተመትተው መገደላቸው ይታወሳል።

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *