የወልዲያ ህዝብ ቁጣ ወደ ሌሎች ቦታዎችም ተዛምቷል ድርጅቶችና መኪኖች ሲቃጠሉ አውቶብሶች ታግተዋል

በወልዲያ ከተማ ከመቀሌ የመጡ የመቀሌ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ፈጽመዋል በተባለው ጸያፍ ስድቦችና
ንግግሮች ምክንያት የተቀሰቀሰው የህዝብ ቁጣ ተባብሶ መቀጠሉ ተሰምቷል።
የታቀደው የእግር ኳስ ጨዋታ ወደ ህዝብ ቁጣና ተቋውሞ ተቀይሮ በርካታ የወልዲያ ነዋሪዎች በመንግስት ታጣቂዎች
እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
በመንግስት ታጣቂዎች እርምጃ ህይወት መጥፋቱን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰአት
ቀጥሏል።
በእለተ ሰንበት በወልዲያ ከተማ የመቀሌና የወልዲያ እግር ኳስ ክለቦች የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸውን እንዲያደርጉ መርሃ
ግብር የወጣ ቢሆንም የመቀሌ ከተማ ክለብ ደጋፊዎች በወልዲያ ከተማ በመኪና እየተዘዋወሩ በድምጽ ማጉያ የህዝብን
ክብር የሚነካ ጸያፍ ቃላት በመሰንዘራቸው ምክንያት በተቀሰቀሰ ግጭት ጨዋታው ሳይደረግ ቀርቷል።
ይህን ጨዋታ ለማካሄድ የሚያስተማምን የጸጥታ ሁኔታ በከተማዋ ስለማይታይ በነዚህ ሁለት ክለቦች መካከል ሊደረግ
የታቀደውን ጨዋታ እንዲሰረዘ መደረጉን የሰሜን ወሎ ዞን ኮምንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልባሴ አሊጋዝ
ተናግረዋል።
የመንግስት ታጣቂዎች በወልዲያ ከተማ አደባባይ በወጡ ነዋሪዎች ላይ የአስለቃሽ ጭስ እና ውሃ በመጠቀም ግጭቱን
ለማብረድና ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ በመቅረቱ ጥይት የመተኮስ እርምጃ ወስደዋል።
ከአገዛዙ ጋር ንኪኪ አላቸው የሚባሉ መኪናዎችና ድርጅቶች በእሳት መንደዳቸውና የመንግስት ወታደሮች እርምጃ
ለመውሰድ ሲጠቀሙበት የነበረ የሆቴል መስታወት በድንጋይ መሰባበሩን የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።
በህዝብና በመንግስት ወታደሮች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ በራያም እንዲሁ ህዝብና የመንግስት የጸጥታ
ሃይሎች ተፋጥጠዋል።
ከደሴ በርካታ ቁጥር ያላቸው የመንግስት ወታደሮች በከባባድ የጦር መሳሪያዎች በመታገዝ በተሽከርካሪ ተጭነው
እየገሰገሱ እንደሆነም ተዘግቧል።
በሃይቅ ተሳፋሪ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ አምስት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶች ጉዞዋቸው ተስተጓጉሎ ታግተው መቆማቸው
ተሰምቷል።
እነዚህ አውቶብሶች ላይ ጥቃት እንዳይፈጸም የመንግስት ወታደሮች ወደ ቦታው በተሽከርካሪ እየገሰገሱ ሲሆን
በሂሊኮፍተርም እያዣንበቡ እንደሆነ ተጠቁሟል።

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *