በወልድያ ግጭት ተቀስቅሷል ሊደረግ የነበረው የመቀሌና የወልድያ እግር ኳስ ክለብ ጨዋታ ተሰርዟል

በእሁዱ መርሃ ግብር መሰረት በወልድያ ከተማ እግር ኳስ ክለብና በመቀሌ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ሊደረግ የነበረው
ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ እክል ገጥሞታል።
በወልድያ ከተማ ከጨዋታው በፊት ከፍተኛ ውጥረት እየተስተዋለ መሆኑንም እየተገለጸ ይገኛል ህንጻዎች ላይ ጥቃት
መድረሱንም የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የመቀሌ ከተማ እግር ኳስ ተጫዎቾች ወደ ወልዲያ ሲገቡ በከፍተኛ የመንግስት ወታደር ታጅበው መግባታቸው ከፍተኛ ቅሬታ እንዳስነሳ ይነገራል።
ከዚህም በተጨማሪ የመቀሌ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት በወልዲያ ከተማ በመኪና
እየተዘዋወሩ በድምጽ ማጉቢያ የህዝብን ክብር የሚነኩ ጸያፍ ቃላቶችን ሲናገሩ መደመጡ ለግጭቱ መነሻ ዋና መንስኤ
እንደሆነ ተጠቅሷል።
የመቀሌ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች በሆቴል ውስጥ በከፍተኛ ጥበቃ ላይ እንደሚገኙ እየተነገረ ይገኛል።
በከተማው የተነሳውን የህዝብ ቁጣ ለማብረድ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መንቀሳቀሳቸውንና እርምጃም እየወሰዱ
እንደሚገኙ ተነግሯል።
በመኪኖች እንዲሁም በሆቴሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ እንደሆነ እየተሰማ ሲሆን በከተማው ውስጥ የጥይት
ተኩስም መሰማቱን ተነግሯል።
የመንግስት ሃይሎች በህዝቡ ላይ አስለቃሽ ጭስ ጥይት መተኮሳቸውንና ህዝቡም አልሞ ተካሽ ሲጠቀሙበት የነበረው
አርሴማ ሆቴል ላይ ጥቃት እንዳደረሱ ተነግሯል።
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በህዝቡ ላይ በወሰዱት እርምጃ የደረሰ ጉዳት እንዳለ ለማረጋገጥ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
በዛሬው እለት ሊደረግ የታቀደው የመቀሌ ከተማ እግር ኳስ ክለብ እና የወልዲያ እግር ኳስ ክለብ የፕሪሚየር ሊግ
ጨዋታ መሰረዙ እየተነገረ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸውን ያካሄዱ ሌሎች ክለቦችንና ውጤቶችንም በስፖርቱ ክፍላችን በዝርዝር
ይቀርባል

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *