በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሌሊቱን ተማሪዎች ሲደበደቡ ማደራቸው ተሰማ

ከወልዲያ አዲግራት፣ ከአዲግራት ወደ ጎንደር፣ ደብረታቦርና አንቦ እየተሸጋገረ የተቀጣጠለው የተማሪዎች አመጽ ወደ አክሱም ተሸጋግሮ ሌሊቱን
የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተደበደቡ ሲሆን በድብደባው የቆሰሉ ተማሪዎች ወደ አክሱም ሪፈራል ሆስፒታል መሄዳቸው ተሰምቷል፡፡
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በሆኑና ከአማራና ኦሮሞ ክልል በመጡ ተማሪዎች ላይ በግምት ከምሽቱ 1-2 ሰአት አካባቢ በተጀመረው ድብደባ ብዙ
ተማሪዎች የተፈነከቱ ሲሆን በድብደባው የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ተማሪዎች ወደ አክሱም ሪፈራል ሆስፒታል ሲወሰዱ ቀሪዎቹ የዩኒቨርሲቲውን
ቅጥር ጊቢ እየለቀቁ በቅዱስ ያሬድ ቤተ-ክርስቲያን ተጠልልው ይገኛሉ ተብሏል፡፡
የተማሪዎችን ግጭት ተከትሎ የመቀሌ ወጣቶች ተቃውሞ ሊያስነሱ ይችላሉ የሚል መረጃ ደርሶኛል የሚለው መንግስት በከተማዋ ላይ የፌደራል፣
የመከላከያና የትግራይ ሚሊሺያ ሰራዊት እንዲሁም አዲስ ምልምል ሰራዊት ከማሰልጠኛ በማውጣት መቀሌ ከተማ ማስፈሩ ተሰምቷል። ሊቀሰቀስ
የችላል ተብሎ የተሰጋው የወጣቶች ተቃውሞ በህወሃት ላይ ያነጣጠሩ ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ የሚል ፍርሃቻ እንደሆነ ተጠቁሟል። ተገኘ የተባለው
መረጃ በህወሃት ላይ ከፍተኛ ስጋት ስለፈጠረ ተቃውሞው አደባባይ እንዳይወጣ ከወዲሁ አፍኖ ለማቆም የተወሰደ እርምጃ መሆኑንም ለማወቅ
ተችሏል፡፡

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *