በሞያሌ የተገደሉ ንጽኋን ኢትዮጵያኖች ቁጥራቸው ሲጨምር ኮማንድ ፖስቱ ግድያው በስህተት ነው ማለቱ ተሰማ

በሞያሌ የመከላከያ ሰራዊት በወሰዱት የሃይል እርምጃ የጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንጽኋን ኢትዮጵያኖችን መግደላቸው እና
ማቁሰላቸው ቁጣን እየጫረ ይገኛል።
የመንግስት ወታደሮች በሞያሌ በሚኖሩ ንጽኋን ኢትዮጵያኖች ላይ በከፈቱት ተኩስ ህይወታቸውን ያጡ ነዋሪዎች ከ 15
በላይ እንደሚደርሱ የሚወጡ ሪፖርቶች ያመለክታሉ። ይሁን እንጂ በወታደሮቹ የጥይት እሩምታ በሞያሌ ከተማ
ህይወታቸውን የተነጠቁት ኢትዮጵያኖች ቁጥራቸው ከዚህ እንደሚያሻቅብ እየተነገረ ይገኛል።
ወታደሮቹ በወሰዱት እርምጃ ከተገደሉት በተጨማሪ በርካታ ንጽኋን ነዋሪዎችም እንደተጎዱ እና እንደቆሰሉ ከቦታው
የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በከተማው ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የእለት ኑሮዋቸውን ሲመሩ በነበሩ ንጽኋን ነዋሪዎች ላይ የመከላከያ ሰራዊቱ በቀጥታ
ተኩስ በመክፈት የህዝብ እልቂት እንዳደረሱ ተነግሯል።
የሞያሌ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ አስቻለው ዮሃንስ በከተማው አዲስ እልቂት እና አለመረጋጋት እንደተፈጠረ በመግለጽ
የእልቂቱ መነሻ እየተጣራ እንደሆነ አሳውቀዋል።
የወታደሮቹን እርምጃ ተከትሎ ወደ ሆስፒታል የመጡት ተጎጂዎች በሙሉ ጉዳቱ የደረሰባቸው በተተኮሰባቸው ጥይት
እንደሆነ የሞያሌ ሆስፒታል ዳይሬክተር ገልጸዋል።
በአጨቃጫቂ ሁኔታ አገዛዙ ጸድቋል ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለመተግበረ የተቋቋመው የኮማንድ ፖስትም
ወታደሮች በንጽኋን ሰዎች ላይ ተኩስ ከፍተው በሞያሌ ከተማ ግድያ እንደፈጸሙ በማሳወቅ ይህ ግን የሆነው በስህተት
ነው በማለት ማስተባበያ ሰጥቷል።
የመንግስት ወታደሮች በሞያሌ ንጽኋን ኢትዮጵያኖችን መግደላቸውን እና ማቁሰላቸውን ተከትሎ ለአገዛዙ እምቢተኝነቱን
እየገለጸ ያለው ህዝብ ቁጣውን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያንረው እየተነገረ ይገኛል።
በቦረና ሞያሌ የመንግስት መከላከያ ሰራዊት በፈጸሙት የግድያ ተግባር ህይወታቸውን ላጡ ንጽኋን ኢትዮጵያኖች
የተሰማንን ሃዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *