ቢረፍድም ዛሬ መጀመር አለበት !!!ከ- አብዶ ኑር የሱፍ – ኖርዌይ ኢሜይል- abnuye2001@gmail.com

  ኧረ በህግ አምላከ እንዳንል በዳይም ፣ከሳሽም ፣ህግ-አውጭም፣ህግ-አስትረጓሚም እና ህግ- አስፈጻሚም አንድ አካል ሆነብን ፡፡ ወዴት እንተንፍሰው ? ለማን አቤት እንበል ? ወያኔ ለ21 አመታት ሀገር በማፍረስ እና በዘር ማጥፋት ተግባር ላይ በማን አለብኝነት መንፈስ እስከዛሬ ተሰማርቶ ቆይቷል ። በሌላ በኩል ሀገረ ወዳድ የሆኑ ንጹሃን ኢትዮጵያዊያኖችን እያሸማቀቀ ፣ እያሳደደ ፣ እየገደለ ብሎም የአሸባሪነት ታርጋ እየለጠፈ ወደ ዘብጥያ በመወርወር ኢትዮጵያ ሀገራችንን በተለመደው ዉሸቱ እና በጉልበቱ የስልጣን ጥማቱን ለማርካት ሲባዝን ይታያል ፡፡ የወያኔ አምባገነናዊ መንግስት በዉሸት የተካነ ፣አፋኝ ፣ገዳይ፣እውነት የሚያሰፈራው እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት እና የታሪክ ጠላት መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው ። የወያኔ አምባገነናዊ መንግስት ሰፊውን የኢትዮጵያ ህዝብ ዐይንህን ጨፍን እያለ ለማታለል የሚሞክርባቸው ትእይንቶች የኢትዮጵያን ህዝብ አንጀት ከማሳረር አልፎ በተደራጀ የማፊያ ቡደን መመራታችን አንገታችንን ካስደፋን ድፍን 21 አመታት አለፉን፡፡ ውድ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ ይህ የማፊያ ቡድን ለረጅም አመታት በከፋፍለህ ግዛው መርህ ሲያሰቃየን የኖረው በወያኔ ጥንካሬ ወይስ በእኛ ደካማነት ? ለዚህ መልስ በወያኔ ጥንካሬ እንደማትሉኝ ግልጽ ነው፡፡ ይህ ውሸትን ሃይማኖቱ ያደረገው የወያኔ አምባገነናዊ ቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ ከስርአቱ የጭቆና ቀንበር እንዳይወጣ እና እኔ አውቅልሀለሁ እያሉ በሚመሩት የውሸት እና የጨለማ መንገድ ብቻ እንዲጓዝ በሚያደርጉት ጥረት ለስርአቱ ታማኝ የሆኑ ፣ ሆዳቸውን የመረጡ በጊዜው አጠራር ሆድ አደሮች እና ወደ ነፈሰበት የሚነፍሱ ግለሰቦችን በመጠቀም ሀገር ማፈራረሱን ፣ የሀገር ወዳድነት ሰሜት ማቀዝቀዙን ፣ የዜጎችን ስነ- ልቦና መስለቡን እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት እና ታሪክ ጠላት መሆናቸውን ቀጥለውበታል ፡፡ ወያኔ ጭፍራዎቹን እና አሽከሮቹን በተለያየ ጥቅማ ጥቅም በማሰር እና የአጃቢዎቹን ቁጥር በማብዛት የሚከተለውን አምባገነናዊ አመራር ህዝባዊ ለማስመሰል ፣ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም የበሰበሰ የፖለቲካ መርዙን ለሰፊው ህዝብ ለማዳረስ እና ህዝቡ ማንኛውንም አይነት የመብት ጥያቄዎችን እንዳይነሳ ከማድረጉ በተጨማሪ ገና ከጅምሩ የሃይማኖት ተቛማቶችን እና አባቶችን በመዳፋቸው ውሰጥ በማስገባት የፖለቲካ መጠቀሚያ ሲያድረግ የነበረው የወያኔ መንግስት አሁንም ይህንኑ ተግባር ዋና ስራው አድርጎ ቀጥሎበታል ፡፡ ይህ እርኩስ መንፈስ የተጠናወተው የወያኔ ቡደን እራሱ ያስቀመጣቸው የእምነት አባቶችን በመጠቀም ሃይማኖቱን የሚያከብረውን እና የሚወደውን የኢትዮጵያን ህዝበ ክርስቲያን እና የሙስሊሙን ማህብረሰብ በቁጥጥሩ ስር በማዋል የኢትዮጵያ ሀገራችንን ታሪክ ማቆሸሽ ብሎም የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ከሚያደርገው መፍጨርጨር በተጨማሪ ወደፊት በቤተ-እምነቶች እና የሃይማኖት አባቶች ላይ ጥቁር አሻራ ጥሎ ለማለፍ እንዲሁም ለእምነት አባቶቻችን ክብር እንዳይኖረን ለማድረግ የሚሰራውን ደባ እኛ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች እጅለእጅ ተያይዘን የሃይማኖታችን ብሎም የምንወዳት እናት ሀገራችን ጠላት የሆነውን ወያኔን በቃህ የምንልበት ጊዜ ቢረፍድም ዛሬ መጀመር አለበት ፡፡ የተነቃበት የወያኔ ሃይማኖትን የመከፋፈል ቁማር ለይስሙላ በተቀመጠው ህገ-መንግስት ላይ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ቢባልም ህጉ-መንግሰቱ እንደ እነ መለስ ዜናዊ እና ሕወሓት ፍላጎት የሚሻር ስለሆነ እጃቸውን በሃይማኖት ዉስጥ ጣልቃ በማስገባት ከዚህ በፊት የክርስትና እና የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያዊያንን ለመከፋፈል በጠነሰሱዋቸው ሴራዎች ምክንያት እንዳንቀራረብ እና የጋራ ችግሮቻችንን በጋራ መፍታት እዳንችል አድረጎ በማስቀመጥ ሀገር የማፍረስ ስራውን በማን አለበኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ከዚህ ቀደም የወያኔ አምባገነናዊ መንግስት የፖለቲካ ኪሳራ ወይም የፖለቲካ ትኩሳት ሲያጋጠመው የህዝቡን ሀሳብ ለማሰቀየር እና ትኩረት ለመሳብ ከሚጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ የነበረው የክርስትና እና እስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን ማጋጨት ነበር ። ወያኔ መስጊድ በማቃጠል ክርስቲያኖች አቃጠሉት እንዲሁም ቤተ -ክርስቲያን አቃጥሎ ሙስሊሞች አቃጠሉት,,,,ወዘተ እያለ እኛ በጎሪጥ እንድንተያይ እና እንደ ጠላት መቀራረብ እንዳንችል ማድረጉ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ፡፡ ይህም ተግባሩ በፍቅር እና በአንድነት የሚኖሩትን የእምነቶቹን ተከታዮች እንደ እግር እሳት ሲያንገበግበን ኖሯል ፡፡ በቅርብ ትውስታችን እንኳን የወያኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ከህዝብ ከመሰወራቸው በፊት 99.6% የወያኔ ካድሬ በታጨቀበት ምክር ቤት ውስጥ ንግግር ሲያደረጉ እንደተለመደው « አንድአንድ አክራሪ ሙስሊሞች በኢትዮጵያ በሸሪአ የሚተዳደር መንግስት መመስረት ፍላጎት ያላችው እንዲሁም ጥቂት አክራሪ ክርስቲያኖች ኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሀገር ብቻ ናት የሚሉ ,,,,, ወዘተ» እያሉ በለመደ አፉቸው የየእምነቱን ተከታዮች እርስ በእርሳቸው እንዳይተማምኑ እና በአንድነት እንዳይቆሙ ለማድረግ ያደረጉትን ሙከራ የሰማ ሰው ከዝንብ ማር አይጠበቅም ብሎ ከማለፍ ሌላ ምን ሊባል ይችላል ? ሰውየው እደለመዱት ለመከፋፈል ቢሞክሩም እኛ የኢትዮጵያ ህዝቦች እናት ሀገራችን የክርስቲያኑም ፣የሙስሊሙም፣የተለያዩ እምነቶችን የሚከተሉ እንዲሁም ምንም እምነት የማይከተሉ ወገኖች የጋራ መኖሪያችን መሆንዋን ጠንቅቀን የምናውቅ ነን ። ወያኔ እና በሃይማኖቶች ላይ ያለው ጣልቃ የመግባት ሱሰኝነት በአጼ መለስ ዜናዊ ሲመራ የነበረው የወያኔ ቡድን በሃይማኖቶች ውስጥ የበግ ለምድ እየለበሰ በመግባት የተኩላ ተግባሩን እያከናወነ ይገኛል ። ይህ የማፊያ

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *