በወያኔ ሰራዊት መካከል ቡሬ ግምባር ላይ ተፈጥሮ የነበረው የእርስ በርስ ውጊያ ዘርን መሰረት ያደረገ እንደነበር ታወቀ::

በቅርቡ በተገባደደዉ የፈረንጆቹ አመት ማለቂያ አካባቢ በቡሬ ግንባር ልዩ ስሙ ማንዳ አየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ የሰፈረዉ የኢትዮጰያ መከላከያ ስራዊት ጎራ ለይቶ እርስ በርሱ የተላለቀዉ ትግርኛ ተናጋሪ በሆነዉ ጦርና በተቀሩት ኢትዮጵያዉያን መካከል በተፈጠረዉ አለመግባባት መሆኑን አዲሰ አበባ ዉስጥ የሚገኙ የግንቦት ሰባት ድምጽ ወታደራዊ ደህንነት ቃል አቀባዮች ታማኘ የሆኑ የመከላከያ ምንጮችን ጠቅሰዉ በላኩልን ዜና ገለጹ። በየትኛዉም ቦታ በሰፈረዉ የኢትዮጵያ ሰራዊት ዉስጥ “የበላይ ነን” በሚሉ ትግርኛ ተናጋሪዎችና በተቀረዉ የሰራዊቱ አባላት መካክል ምን ግዜም ቢሆን ዉጥረትና ትናንሽ ግጭቶቸ የሚከሰቱ ሲሆን የቡሬዉን ግጭት ልዩ የሚያደርገዉ በርከት ያለ ቁጥር ያላቸዉና መሳሪያ የታጠቁ የሰራዊቱ አባላት ለትግራይ መኮንኖቸ አንታዘዝም ወይም የትግራይ አዛዦቸ አያዝዙንም ብለዉ በፈጠሩት ግጭት ቁጥራቸዉ ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ ወታደሮቸ ላይ የሞትና የአካለ ጉዳት በመድረሱ ነዉ።

በቡሬ ግንባር የተፈጠረዉ የእርስ በርስ ወታደራዊ ግጭት ዜና በሌሎቸ የአገሪቱ አካባቢዎቸ እንዳይሰማ የወያንኔ አገዛዝ ክፍተኛ ጥንቃቀ ቢያደርግም የኢትዮጵያ ሳተላይት ተlቪዥንና ሬድዮ አገልግሎቶች ግጭቱ በተፈጠረ በደቂቃዎቸ ዉስጥ ዘናውን በመላዉ አለም ማሰራጨት አንደቻለ ለማወቅ ተችሎአል። ስለሆነም ዛሬ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በብዛት በሰፈረባቸዉ የአገሪቱ አካባቢዎቸ ሁሉ ሰራዊቱ በትግርኛ ተናጋሪዎችና ለትግራይ ወታደራዊ አዣዦች አንታዘዝም በሚሉ ሁለት ትላልቅ ጎራዎች ተከፍሎ ከፍተኛ ፍጥጫ ዉስጥ በመግባቱ የወያኔው አገዛዝ ክፉኛ እንደተደናገጠ ከየቦታዉ የሚደርሱን ዜናዎች ያስረዳሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዘ በቡሬ ግንባር ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ወታደሮች ያሰር ሲሆን ለግምገማ ትፈለጋላችሁ በሚል ሰበብ አራት ሻለቃ ጦር ትጥቅ አስፈትቶ ወታደሩን እያንገላታ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። ከአንድ ሳምንት በላይ የፈጀዉና አሰልቺዉ የወያኔ ግምገማ የተገባደደ ቢሆንም በቡሬ ግንባር ከሚገኘዉ የመከላከያ ሰራዊት ዉስጥ አራት ሻለቃ ጦር አሁንም ትጥቁን ፈትቶ በወያኔ ካድረዎች አጥንት የሚስብር ዘለፋና ዛቻ እየደረሰበት መሆኑን ለግንቦት ሰባተ ድምጽ ዝግጅት ክፍል ስልክ እየደወሉ የተናገሩ የሰራዊቱ አባላት ገልጸዋል። ይህ የሰራዊቱ አባላት ከግንቦት ሰባት ጋር የሚያደርጉት የስልክ ግንኙነት ያበሳጨዉ ወያነ በቡሬና በአካባቢዉ የስልክ ግንኙነት እንዲቋረጥ ማድረጉ የሚታወስ ነዉ።

በለሌ በኩል ደግሞ ወያነ “ሽብርተኞችን “ ትረዳላችሁ ወይም “ክሽብርተኞች “ ጋር ትገናኛላችሁ  በሚል በቡሬና በለሎችም የአገሪቱ የጠረፍ አካባቢዎች የሰፈሩ ወታደሮቸን  ትጥቅ እያስፈታ ማሰር መጀመሩን ለዝግጅት ክፍላችን በተከታታይ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደ ሰደድ እሳት በመቀጣጠል ላይ ያለዉ ጸረ ወያኔ እንቅስቃሴ ያስደነገጠዉ ወያኔ የነጻነት ህይሎችን ይቀላቀላሉ ብሎ የጠረጠራቸዉን ወታደሮቸ በየቀኑ እስር ቤት እየወረወረ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።ይህንን በተመለከተ ከፍተኛ ወታደራዊ ችሎታና ልምድ ያላቸዉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር አባላትና በመከላከያ ኢንጂነሪንግ የሰለጠኑ ወጣት መኮንኖች ከየቦታዉ በስምና በዘር እየተመረጡ በመታሰር ላይ ናቸዉ። ባጠቃላይ ወያነ በአሁኑ ወቅት ከትግርኛ ተናጋሪዎች ውጭ በሌሎች የሰራዊቱ አባላት ላይ ምንም አይነት እምነት እንደለለዉ በሚወስዳቸዉ እርምጃዎች ያሳየ ሲሆን ይህንን የተረዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አጋጣሚውን ባገኙ ግዜ ሁሉ የታጠቁትን መሳሪያ እንደያዙ የነጻነት ሀይሎችን በመቀላቀል ላይ መሆናቸዉን ከየቦታዉ የሚደረሱን ዘናዎቸ ያስረዳሉ።

ለየት ባለና በዛረዉ ቀን በደረሰን ዜና መሰረት ዘረኛዉ የወያነ አገዛዝ የ “ነኢሰን” ወይም በሙሉ ቃሉ የነጻ ኢትዮጵያ ሰራዊተ ንቅናቀ አባላት ናችሁ የሚላቸዉን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከየጦሩ ሰፈር እየሰበሰበ በማሰር ላይ መሆኑን የግንቦት ሰባት ድምጽ ዘጋቢዎች ወታደራዊ ምንጮቸን ጠቅሰዉ በላኩልን ዘና ገለጹ። ነኢሰን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከህወሀት መሳሪያነት ተላቅቆ የአገርና የወገን አለኝታ እንዲሆን የሚታገልና ኢትዮጵያ ሰራዊት ዉስጥ የበቀለ ንቅናቀ ነው። ነጻ ወይም ነጻነት የሚለው ቃል ከራሱ ስም ዉጭ ሌላ የትም ቦታ እንዲሰማ የማይፈልገው ህወሀት ግን ነኢሰንን ገና ከመፈጠሩ ማጥፋት አለብኝ በሚል

ሻ/ቃ ቃለአብ ከበደ

ሻ/ቃ ሰለሞን አለሙ

ሻ/ቃ ታቦር ኢዶሳ

ሻ/ቃ ተረፈ ማሞ

ሻ/ቃ ኪሲ ጎበሹ

ሻ/ቃ ሞገስ መለሰ

ኮሎነል ሙሉገታና ሻለቃ አስረስ

የሚባሉ ስምንት የአማራና የኦሮሞ ስም ያላቸዉን ከፍተኛ መኮንኖች ከያሉበት ሰብስቦ የረጂም ግዘ አገልግሎታቸውን በመሰረዝ ያለጡረታ ከሰራዊቱ እንዲባረሩ አደርጎአል

posted by issa abdusemed

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *