ዜና ሰበር በአዲስ አበባ ከተማ ቁጥራቸው:ከ 27 በላይ ህንጻዎች ሊፈርሱ ነው::

በአዲስ አበባ ከተማ ቁጥራቸው:ከ 27 በላይ ህንጻዎች ሊፈርሱ ነው:: ለቀላል የባቡር ፕሮጀክት እና የመንገድ ማስፋፍያ ; ስራ :በአዲስ አበባ ቁጥራቸው ከ 27 በላይ ህንጻዎች እንደሚፈርሱ… :መንግስት ይፋ እንዳይሆን ያልፈለገው :ቀዳማይ ፕላን ;በፕሮጀክቱ ጽ/ቤት እንደሚገኘ:ከድርጅቱ አካባቢ ሾልከው የወጡ የዜና ምንጮች አጋለጡ::እነዚሁ ሾልከው የወጡ ማስረጃዎች እንደሚሉት…..ከ አያት ጨፌ ..መገናኛ :በመስቀል አደባባይ አድርጎ እስከ ጦር ሃይሎች እና….ከቃሊቲ መስቀል አደባባይ …በመሃል ጎዳናዎች ላይ ይዘረጋል የተባለው እና ስራ መሰረቱ የተጀመረው :የቀላል የባቡር ፕሮጀክት ስራ :በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ለሚያጋጥመው የመንገድ ጥበት :ስፋት ይረዳ ዘንድ :የህንጻዎቹ መፍረስ ግድ እንደሆነ እና የ ማፍረሱም ስራ የተጀመረው ፕሮጀክት 50 በመቶ ሲጠናቀቅ ሊሆን እንደሚችልም ሾልኮ የወጡት የዜና ምንጮች ያስረዳሉ:::ከሚፈርሱት ህንጻዎች ውስጥ ከሁለት ያላነሱ :በኪራይ ቤቶች አስተዳደር የሚተዳደሩ የመንግስት :ባንቢስ አካባቢ የሚገኝ :የ ሉተራውያን ይዞታነት ስር የሚገኝ ህንጻን ጨምሮ :በ ርካታ በግለሰብ ይዞታነት ስር የሚገኙ ከ 6 አመት በላይ እድሜ የሌላቸው አዲሶች እና አሁንም ድረስ በግንባታ ላይ ያሉ ህንጻዎች እንደሚሆኑም :እነዚሁ ዘገባዎች ጨምረው ይገልጻሉ:: አገዛዙ ለሚፈርሱት ህንጻዎች : ተመጣጣኝ የሆነ የካሳ ክፍያ በወቅቱ ያድርግ አያድርግ ወይንም አቅሙ ይኑረው አይኑረው : ነገሩን በሚስጥርነት ከመያዙ ውጪ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም:: ይሀው ይሰራል የተባለው የቀላል ባቡር ፕሮጀክት: ፕላን :ታሪካዊ ሃውልቶችንም ጭምር ከቦታቸው ያፈናቀለ እና የመኖር ህልውናቸውን ጥያቄ ውስጥ ሚያስገባ እንደሆነ ሌሎችም አማራጭ ፕላኖች እንዳሉዋቸው እና አገዛዙ እጁን ሃውልቶቹን ከመነካካት እንዲታቀብ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ሲሰሙ እንደነበር ይታወቃል::

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *