አሥራ አንድ ሰዓታት የፈጀው ክርክር (ክፍል 2) – (አቶ ሃብታሙ አያለው – የአንድነት ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ)

እንደ መግቢያ
ቅጥፈት የስብዕና መሽርሽር ምልክት ነው፡፡ የግለሰቦች ስብሰብ በሚፈጠረው ማህበረሰብ ውስጥ የስብዕና መሸርሸር ሲበራከት ማህረሰበባዊ አደጋ ሰላማዊ አኗኗሩን ማነዋወጥ ይጀምራል … ማህበራዊ ቀውስ በሰፈነበት ደግሞ ከግለሰቦቹ ውድቀት የሚነሳው ገፊ ምክንያት እንደ ማህበረሰብ የተገነቡ የጋራ እሴቶችን ይንዳል፡፡ ባህል ፤ ሃይማኖት ፣ታሪክ ፣ወግ እና ልማዶች ሁሉ መሰረታዊ ይዘታቸውን የላቁና የሰው ልጅ እንደ እንስሳ በቀላሉ ከእንቱ ነገሮች ጋር ሲወዳጅ ይስተዋላል፡፡

ቅድስ መጽሐፍ “በተቀደሰው ስፍራ የጥፋትነ ክርኩስት ባያችሁ ጊዜ አንባ ያስተውል” እንዳለ ለዘመናት የተገነባ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ተንዶ ግብረ ሰዶማዊነት፣ ሱሰኝነት ፣ሙሰኝነት ገዳይነት ከፍ ያለ ስፍራ ሲቸራቸው ሰብዓዊነት (የሞራል ልዕልና) ምን ትርጉም ይኖረዋል?
ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች እንደ ከዋክብት ሲበዙ ‹በድሪም ላይነሩ› በሰማይ በራሪ፤ በፈጣኑ ባቡር በምድር ተሸከርካሪ፤ ባህር ውቅያኖስ ተሻጋሪ፡ ለመሆን ሀገር ተገልብጣ ፈርሳ ብትሰራ ያለሰብዓዊ ልማት ትርጉም አልባ ናት

ሀገር ያለ ሰው ሰውስ ያለ ሀገር እንደምን ይሆናል? ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ‹‹ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤ ሀገር ውስብሰብ ነው ውሉ›› እንዳለ፡፡ እንዲሁ ነው፡፡ የገዛ ዜጎቹን ለማምከን በሃሳብ በመለየታቸው እየወነጀለ፤ ዘብጥያ እየጣለ፤ ከሀገር እያሰደደ፤ በተከፈተ የሞተ ላንቃ ከወረወረ፤ በስነ ምግባር የታነፀ ብቁ እና ጤናማ የሰለጠነ ትውልድ እንዲፈጠር ከመጣር ይልቅ በተቃርኖ ጫፍ ከተሰለፈ፤ እንኳን መሬቱን ስማዩን ቢያለማው እንደምን መንግስት ብለን ልንጠራው እንችላል?

የአንድ ሀገር መንግስት ተነግሮት ካላደመጠ፤ ተናግሮ ካልተደመጠ ወንበሩ ለጥፋት እንጂ ለልማት አይጠቅመውም፡፡ መሪዎች በህዝባቸው ላይ ቅጥፈት ከጀመሩ ወገን ለይተው ከቦደኑ፤ ከዕውቀት እና ከጥበብ እርቀው የጉልበት አገዛዝ ካሰፈኑ፤ እመነኝ የመቃብራቸው ቀን ይረዝም ይሆናል እንጂ ሞታቸውን ለማወቅ መርዶ ነጋሪ አያሻህም፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት (አሥራ አንድ ሰዓታት የፈጀው ክርክር) በሚል ለንባብ ያቀረብኩትን የውዝግብ ውሎ የመሪዎቻችንን ቅጥፈት በማስቀደም ያቀረብኩትን አጠቃላይ ቅኝት በዚህ ከፍል አጠናቅቃለሁ ፡፡

ከማለዳው የሻይ እረፍት በፊት (በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጆርናሊዝምና ኮምኒኬሽን ት/ት ቤት መምህር) የሆኑት ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ ያቀረቡት የጥናት ይዘት በመጠነኛ ፍርሃት የተወላከፉ ሃሳቦች ቢደመጡበትም አብዛኛው የጥናታቸው ክፍል ጥሩ ሊባል የሚችል (academic discourse) እንደ ነበር አመላክቻለሁ ፡፡

ነገር ግን ዶ/ር አብዲሳ በመክፈቻ ስነ- ስርዓቱ ሁለተኛ ተናገሪ ሆነው ካስሙት ወሳኝ ንግግር መካከል ጥቂቱን ሳይጠቅሱ ማለፍ የዕለቱ ዋና ተናጋሪ የነበሩት የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ ካደረጉት ፍሬ አልባ ንግግር ጋር ወደ ቅርጫቱ ለመጣል የማሰብ ያህል ስለተሰማኝ ጥቂት እጠቅሳለሁ ፡፡
• ቁጥራቸው የበዛ ስብሰባ ብናደርግም ለውጥ አላመጣንም !
• ሁሉ ጊዜ የሚዲያ ተሳታፊዎቻችን ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ናቸው፡፡
• የተለየ አስተሳስብ የሚያነሱትን ለማስወገድ ከመጣደፍ በቀር ሃሳብ ለመቀብል ዝግጁነት አይታይብንም፡፡
• እኛ ትክክል ነን እነሱ ትክክል አይደሉም ብሎ መነሳት ሃሳብ አፍላቂዎችን ስለሚያገልል የሚይጠቅም አመለካከት መሆኑን መገንዘብ ይገባናል፡፡
የሚሉ ነጥቦችን ከጠቃቀሱ በኋላ የጥናት ሰነዳቸውን ሲያብራሩ ደግሞ………
• ዶሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግስት ለመሆን በአነድ አቅጣጫ የሚጓዝ ረጅም ጊዜ ሚወስድ ሥርዓት መዘርጋት ይጠይቃል፡፡ በኢትዮጵያ የመፃፍ፤ የመናገር፤ የነፃነት፤ የተለያየ የፖለቲካ አስተሳሰብ የማራመድ ጥያቄ እያለ፤ በየአምስት አመቱ የመንግስት ለውጥ ለማድረግ ምርጫ የሚደረግበት ሥርዓት ባለበት ሁኔታ ልማታዊ መንግስት ማለት በእጅጉ አዳጋች ነው፡፡
• የመንግስት እና ፓርቲ መዋቅር ስላልተለያየ ሁሉንም ኢህአዴግ ስለተቆጣጠረ አንጂ አንድ ሁለት ክልሎች ሌላ ፖርቲ ቢያሸንፍ ሥርዓቱ እንዴት ሊቀንጥል ይችላል? አንኳር በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች እንኳን መግባት ባልተፈጠረበት ሁኔታ፤ እኔ ከስልጣን ከወረድኩ ሌላው መጥቶ ያፈረሰዋል በሚል ስጋት ስልጣን የሞት ሽሪት ጉዳይ ስሚሆን ከአምባገነንነት ወጪ ሌላ አማራጭ ሊኖር አይችልም፡፡ ሲሉ ጥሬ ሃቁ ላይ ደፈር ሲሉ ተስተውለዋል

ሌላኛው ጽሁፍ አቅራቢ አቶ ሙሼ ሰሙ በበኩላቸው ባመዛኙ ከዶ/ር አብዲሳ ጋር የሃሳብ አንድነት ነበራቸው ማለት ይቻላል ፡፡ አቶ ሙሼ ጠንከር ባሉ ቃላት ‹‹ልማትዊ የሚለው የአህአዴግ አጀንዳ ከማደናገሪያነት የዘለለ ትርጉም የለውም›› ሲሉ ከደመደሙ በኋላ ‹‹በእኔ እምነት ልማታዊ ያልሆነ መንግስት የለም፤ የአንድ ሀገር መንግስት የዕለት ተዕለት ስራ ልማት ነው፡፡ መንግስታት ከዚህ ውጪ ምን ተልዕኮ አላቸው? የፖለቲካ ፍስፍና እና ስልት ነው ከተባለ ዴሞክራሲያዊነት የሚለውን ቀልድ ትቶ ዳቦ እንሰጣችኋለን መብትና ነፃነት አትጠይቁን ብሎ በግልፅ መምጣት ነው፡፡ ነፃነትን የዳቦ ተከታይ ማድረግ ደግሞ የአቶ መለስ አቋም ነበር ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

አቶ ሙሼ የልማታዊ መንግስት ፅንሰ ሃሰብ አፍኝ ባህሪ ምን እንደሚመስል ከዘረዘሩ በኋላ ትኩረታቸውን ወደ ዕለቱ ርዕስ በማድረግ
• ይህ የምትሉት የልማታዊ መንግስት ባህሪ አጠቃላይ የህዝብን አመለካከት በአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ዕምነት ላይ በማጠር በዚያ ማለፍን አስገዳጅ አድርጎ ያመጣል፡፡ ልማታዊ ጋዜጠኛ፤ ልማታዊ ቄስ፤ ልማታዊ ሼክ ወ.ዘ.ተ… የሚባለውም ከዚህ ጠቅላይ ባህሪ በመነሳት ነው፡፡
• ገና በጠዋት ኢህዲግን በመንግስት ወንበር ሲቀመጥ ለሚድያው ነፃነት ስጥቶ ደርግና ከሱ የቀደሙትን ሊያስወግዝ ደፋ ቀና ሲል ሚድያው ፊቱን ወደራሱ አዙሮ ትችት እንደ ሃምሌ ዝናብ ሲያወርድበት መጠለያ መፈለግ ሳይሆን አማራጭ ያደረገው ከምንጩ ለማድረቅ ሚዲያዎችን ወደ ማፍን መሸጋገር ነበር፡፡
• በተለይ ከሚዲያ ነፃነት አንፃር ይህ ሥርዓት ስለ ልማት ብቻ ወይም ስለ አህአዴግ ብቻ ከሚናገር አዝማሪ ጋዜጠኛ በቀር ሌሎችን ወደ አንድ ጥግ የገፋ የተበላሸ ሥርዓት ነው፡፡ ሲሉ አጥበቀው ኮንነዋል፡፡ የፕሬስ አዋጅ፤ የፀረ ሽብር አዋጅ እና የመሳሰሉት አፍኝ ህጎችም ህግን ለማፈኛ ከመጠቀም የመነጩ ከኢህአዴግ ባህሪይ የተቆዱ ናቸው ሲሉ አውግዘዋል ፡፡
የፎርችኑ ታምራት ገ/ጊዮርጊስ መከራከሪያም በይዘቱ ከዚህ የተለየ አልነበረም፡፡
• የእኔ የአስተሳሰብ ልዕልና ከሁሉም ስለሚበልጥ ሌላውን ከውግዘህ ከኔጋር ተሰለፍ እንባላለን፡፡ እሱን አንቀበልም ስንል ተወግዘን እንለያለን፡፡ ችግር የሚዘንብብንም በዚያ ጊዜ ነው፡፡
• ችግሩ ህግ- መንግስቱ እንደዚያ ሆኖ እንዲጸድቅ ያደረጉ ሊበራል አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች በሌሎች ተደፍቀው በተለያየ አስተሳሰብ ህግ- መንግስቱ መሸርሸሩ ነው፡፡ ከህግ በስተጀርባ መብት የሚጥሱ ሌሎች ህግች እንዲወጡ ተደርጎ የሚዲያ ነፃነት እየተገፈፈ ነው፡፡
• በእኔ ግምት ይህ ህግ- መንግስት የመሸርሸርና የመጣስ የሊበራል ኢለመንቶችን የማጥፋት ዘመቻ ሲጠናከር ልማታዊ መንግስት የሚል ሃሳብ በማምጣት አፈናው የቀጠለ ይመስልኛል ፡፡ ወ.ዘ.ተ የሚሉት ከታምራት ንግግሮች ጥቂቶቹ ነበሩ፡፡

ከዚህ በኋላ በዕለቱ መሪ ሃሳብ ይዘው በዋሉት በዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እና በአቦይ ስብሃት፤ በአቶ ዛዲግ (የኢህአዴግ ተወካይ)፤ በዚህ ፅሁፍ አቅራቢ (የአንድነት ፓርቲ ተወካይ) እና በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በኩል ሰፊ የሃሳብ ንትርክ ተደርጓል፡፡

የኢህአዴግ መሪዎች የአደባባይ ቅጥፈት ጎልቶ የተስተዋለው በዚህ ክፍል ጊዜ ነበር፡፡ አቦይ ስብሃት ከዚያው ከኢአዴግ ባልደረቦቻቸው እንኳን ያልታርቀ የተለመደ አወዛጋቢ ሃስብ ሰነዘሩ፡፡ ”ልማታዊ መንግስት ዛሬ ያመጣነው ሃሳብ አይደለም ገና ጫካ ሳለን ሁለት የሚያጠና ቡድን ልከን ሊብራሊዝምና ሶሻሊዝምን አጥንተን ለኢትዮጵያ እንደማይበጅ ካረጋገጡልን በኋላ ልማታዊ መንግስት የሚለውን ፅንሰ ሃሳብ ይዘን መጣን፡፡”

ይህንን የአቦይን ንግግር ተከትሎ የልማታዊ መንግስት ከ1992 በኋላ የህወሃትን መሰንጠቅ ተከትሎ የመጣ ስለመሆኑ የራሳቸውን ሰነድ እየጠቀስን ተሟገትን፡፡ ዶክተር ዳኛቸው የስርዓቱ በተራ ውሸት ላይ መመስረት የደረስንበትን አሳፋሪ ሁኔታ ያሳያል ሲሉ ጀምረው ላደረጉት ረጅም ንንግር ቤቱ አጸፋውን በደማቅ ጭብጨባ መልሶላቸዋል፡፡ ይህን ጊዜ ዶ/ር ነጋሶ በ”ማንያርዳ የቀበረ ” አባባል የአቦይን ውሸት ተጋፈጡት፡፡ ”ለ10 ዓመታት በፕሬዝዳንትነትና በኦህዴድ አመራርነት ስቆይ ልማታዊ የሚል ነገር የሰማሁት የህወኃትን መሰንጠቅ ተከትሎ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ከጫካ መጣ የሚባለው ውሸትነው፡፡ ደግሞስ ልማታዊ እንሁን ስንል የልማቱ ጸር የሆኑትን ተቃዋሚዎችን ልናጠፋ ይገባል ተብሎ ነበር የቀረበው፡፡ የአሁኑ ልማታዊነት በተቃዋሚዊ ፓርቲዎች ላይ ምን ለማድረግ አስቦ ነው ዴሞክራሲ እየተባለ ያለው፡፡” አሉና እርፍ አረጉን፡፡

የፋናው ስራአስኪያጅ አቶ ወልዱ፤ ከህዳሴው ግድብ ጽ/ቤት አቶ ዛድግ፤ ከኢትዮጵያ የሠላም ኢንስቲትዮት አቦይ ስብሃት፤ ከመንግስት ኮምኒኬሽን ሚንስትር ድኤታው አቶ ሽመልስ ከማል፡ በርካታ ጥረት ቢያደርጉም በሃሳብ የበላይነት ድርጅታቸውን በሃሳብ የበላይነት ከፍ አድርገው ለመውጣት አልተቻላቸውም፡፡ እንደ ተለመደው እያደገች፤ እየተመነደገች ያለች ሀገር፤ የሚድያ ነፃነት የተከበረባት፤ አንድም ዜጋ በአመለካከቱ ያልታሰረባት ሀገር ናት ሲሉን የውሽት ካብ መፈርሱ ባይቀርም ለጊዜው በገዛ መሬዎቻችን ስንዋሽ በሚፈጠር መጥፎ ስሜት ሳያበግኑን አልቀሩም፡፡

መውጫ
አቶ ሽመልስ የውይይቱን መጠናቀቅ የሚያበስር ንግግር ሲያደርጉ የሰነዘሩት ሃሳብ ስንወያይ ብቻ ሳይሆን ስንወጣም እንዲገርመን የፈለጉ ይመስል ነበር፡፡ ‹‹በዚህ ሀገር ብሔራዊ መግባባት ያስፈልጋል፡፡ ዩኒቨርስቲውም የመግባቢያ ፍሬም ወርክ እና ተደጋጋሚ የውይይት መድረክ ሊያዘጋጅ ይገባል፡፡›› ሲሉ ከወትሮ ቁጡነታቸው የተለየ የአነጋገር ዘዬ በመጠቀም ጭምር አጠናቅቀዋል፡፡ ወይ አቶ መለስ በስንቱ 1609626_590403497711255_978655788_n

ጭንቅላት ላይ ቆመው ነበር ለዚህ አስከፊ ሆኔታ የዳረጉን?

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *